መዝሙር 126 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምከምርኮ በደስታ ስለ መመለስ የቀረበ ምስጋና 1 እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ ባመጣን ጊዜ ሕልም እንጂ እውነት አልመሰለንም ነበር። 2 አፋችን በሳቅ ተሞላ፤ አንደበታችንም የደስታ መዝሙር ዘመረ፤ በዚህም ምክንያት አሕዛብ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” አሉን። 3 በእርግጥም ብዙ ታላላቅ ነገሮችን አድርጎልናል፤ እጅግም ተደስተናል። 4 እግዚአብሔር ሆይ! ዝናብ ለደቡብ በረሓ ወንዝ ውሃን እንደሚሰጥ የተማረከብን ሀብታችንን መልስልን። 5 በእንባ የሚዘሩ የደስታ መዝሙር እየዘመሩ ይሰበሰባሉ። 6 ዘሩን ተሸክመው ሲሄዱ ያለቅሱ የነበሩት፥ በደስታ እየዘመሩ ነዶአቸውን ተሸክመው ይመለሳሉ። |