Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 100 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


የምስጋና መዝሙር

1 በምድር ላይ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር “እልል!” በሉ!

2 እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት! የደስታ መዝሙር እየዘመራችሁ ወደ እርሱ ፊት ቅረቡ!

3 እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ የፈጠረን እርሱ ነው፤ እኛ የእርሱ ነን፤ ስለዚህ እኛ እንደ በጎች መንጋ የሚያሰማራን ሕዝቦቹ ነን።

4 እያመሰገናችሁ በመቅደሱ በሮች ግቡ፤ ምስጋናም በመስጠት ወደ አደባባዩ ሂዱ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም አወድሱ።

5 እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩና ታማኝነቱ ዘለዓለማዊ ነው።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች