Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


ሀብትና አጉል ድፍረት

1 በሀብትህ አትመካ፤ ሀብቴ ይበቃኛል አትበል፤

2 የልብህን ፈቃድ ለመፈጸም በስሜትህ ና በጉልበትህ አትመራ።

3 እግዚአብሔር በርግጥ ይቀጣሃልና፥ “በኔ ላይ ሥልጣን የሚኖረው ማነው?” አትበል።

4 እግዚአብሔር ትዕግሥት ትልቅ ነውና፥ “ኃጢአት ሠራሁ ምን መጣብኝ?” አትበል።

5 በበደል ላይ በደል እየከመርህ፥ ይቅርታ አገኛለሁ ብለህ እርግጠኛ አትሁን።

6 “ኀዘኔታው ታላቅ ነው፤ ኃጢአቶቼንም ይቅር ይልልኛል” አትበል።

7 ሳትዘገይ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፤ ነገ ከነገ ወዲያ እያልህ ቀኑን አታራዝም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቁጣ በድንገት ከተፍ ይላል፤ በቅጣት ቀን ትደመሰሳለህ።

8 አላግባብ በተገኘ ሀብት አትመካ፤ በመከራ ቀን ለምንም አያገለግልህም።


ግልጽነትና ራስን መሆን

9 በመጣው ነፋስ ሁሉ አትነፈስ፤ ባገኘኸው መንገድ ሁሉ አትሂድ። በሁለት ምላስ እንደሚናገረው ኃጢአተኛ አትሁን

10 በእምነትህ ጽና፤ በቃልህ ታመን፤

11 ለመስማት የፈጠንክ፥ ለመልስ የገዘገየህ ሁን።

12 ጉዳዩ ከገባህ ለጐረቤትህ መልስለት፤ አለበለዚያ እጅህን በአፍህ ላይ አድርግ።

13 ክብርም፥ ውርደትም ከንግግር ይገኛል፤


ምላስ የባለቤቷን ውድቀት ታስከትላለች።

14 የሐሜተኛ ዝነኝነት ይቅርብህ፤ በምላስህ የሐሜት ወጥመድ አትዘርጋ፤ በሌላ ላይ እፍረት እንደሚወድቅበት፤ በአታላይ ሰው ላይም ብርቱ ፍርድ ይወድቅበታል።

15 ከታናናሾችም ሆነ ከታላላቆች፤ ስሕተቶች ተጠንቀቅ፤

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች