Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


ኢዮስያስ

1 የኢዮስያስ ትውስት፥ በሽቶ ጠማቂው ጥበብ እንደተቀመጠ ዕጣን መዓዛው አይጠፋም፥ ለሁሉም አፎች እንደ ማር የሚጣፍጥ፥ በወይን ጠጅ ግብዣም ላይ እንደሚሰማ ጣዕመ ዜማ ነው።

2 ሕዝቡን ለመለወጥ ትክክለኛውን መንገድ መርጧል፥ አስከፊ የሆኑትን በደሎችም ነቃቅሎ ጥሏል።

3 ልቡን በጌታ ላይ አሳረፈ፤ በክሕደት ወቅት ለሃይማኖት በጽናት ተሟገተ፥ የመጨረሻዎቹ ነገሥታትና ነቢያት፥

4 ከዳዊት፥ ከሕዝቅያስና ከኢዮስያስ በቀር፥ ሁሉም ጥፋትን በጥፋት ላይ ከመሩ፥ የልዑል እግዚአብሔርን ሕግ ዘነጉ፤ የይሁዳ ነገሠታት ጠፉ።

5 ሥልጣናቸውን ለሌሎች፥ ክብራቸውንም ለውጭ፥ መንግሥታት አሳልፈው ሰጥተዋልና።

6 የተመረጠችው ቅድስት ከተማ በእሳት ጋየች፤ መንገዶቿ ባዷቸውን ቀሩ።

7 በእናቱ ማሕፀን ሳለ ለነቢይነት የተቀደሰ ቢሆንም፥ ለመቆራረጥ፥ ለማሠቃየት፥ ለማጥፋት ብቻ ሳይሆን፥ ለመገንባትና ለመትከል ቢመረጥም፤ እነርሱ ግን በድለውታልና ኤርምያስ ይህን ቀድሞ ተንብዮአል።

8 አምላክ ከታላላቆቹ፥ ከኪሩቤልና ከሱራፌል ሠረገላ በላይ፥ ያሳየውን የክብር ራእይ ያየው ሕዝቅኤል ነበር።

9 ዶፍ የወረደባቸውን የጠላት ወታደሮች በመጥቀሱ ትክክለኛውን መንገድ የተከተሉትን ጠቅሟልና።

10 ዐሥራ ሁለቱን ነቢያት በተመለከተ ደግሞ ያዕቆብን በማጽናናታቸው እና በተስፋና በእምነትም እርሱን በመቤዣቸው አጥንታቸው ከመቃብር በላይ ዳግም ያብብ።


ዘሩባቤልና ኢያሱ

11 ዘሩባቤልን እንደምን ከፍ ከፍ እናድርገው? በቀኝ እጅ እንደሚደረግ የቀለበት ማኀተም ነበር፥

12 የዩሴዴቅ ልጅ ኢያሱም እንዲሁ ነበር። በኖሩበትም ዘመን የእግዚአብሔርን ቤት አሠሩ፥ ዘላለማዊ ክብር ያለውን፥ ለእግዚአብሔር የተቀደሰውንም ቤተ መቅደስ አቆሙ። ነህምያ

13 የነህምያ መታሰቢያው ታላቅ ነው፥ የፈረሰውን ግንብ የገነባ፥ ባለ ቁልፍ መዝጊያዎችን የሠራ፥ ቤቶቻችንንም ዳግም ያነጸ እርሱ ነው።


ትውስታ

14 ሄኖክን የሚስተካከል በምድሪቱ አልተፈጠረም፥ እርሱ ከመሬት ተወስዷልና።

15 እንደ ዮሴፍ የመሰለም ከዚህ በፊት አልተወለደም የወንድሞቹ መሪ፥ ሕዝቡንም የደገፈ ነውና፥ አጥንቶቹ መጐብኘትን አግኝተዋል።

16 ከሰዎች ሁሉ የተከበሩት ሴምና ሴት ነበሩ፥ ከሁሉም ሕያው ፍጡር የበለጠው ግን አዳም ነው።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች