Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


ግብዣዎች

1 የክብር እንግዳ አድርገውሃልን? ብዙም አትኩራራ፥ ባሕርይህ ከሌሎች ተጋባዦች አይለይ፥ የሚፈልጉትን ሁሉ እንዳገኙ አረጋግጠህ ተቀመጥ።

2 ኃላፊነትህን ከተወጣህ ወደ ቦታህ ተመለስ፤ የእነርሱ ደስታ ላንተም የደስታ ምንጭ ነው፤ ስለ መልካም ተግባርህም አክሊልን ትቀዳጃለህ።

3 ሽማግሌ ሆይ! ተናገር፤ ትናገርም ዘንድ ይገባሀል፤ ንግግርህ ግን ግልጽነት ይኑረው፤ ዘፈኑንም አታበላሽ።

4 አንዱ ሲያዜም ጣልቃ አትግባ፤ ተገቢ ባልሆነ ሰዓት ጥበብህን ለማሳየት አትሞክር።

5 በወይን ጠጅ ግብዣ ላይ የሚታየ የሙዚቃ ትርኢት፥ በዕንቁ ላይ እንዳረፈ ወርቃማ ፈርጥ ነው።

6 ከምርጥ የወይን ጠጅ ጋር የሚኮሞክሙት ሙዚቃ፥ ወርቃማ መደብ እንዳለው የከበረ ደንጊያ ነው።

7 አንተ ወጣት! መናገር በሚገባህ ወቅት ተናገር፤ ቢበዛ ሁለት ጊዜ እርሱንም ከተጠየቅህ ብቻ አድርገው።

8 ፍሬ-ሐሳቡን ብቻ ለመግለጽ ሞክር፥ በጥቂት ቃላት ብዙ መልእክት አስተላልፍ፤ ብዙ የምታውቅ፥ ንግግር ግን የማትወድ እንደሆንክ ሁነህ ቅረብ፤

9 ታላላቅ ሰዎን እንደ እኩዮችህ አትመልከት፤ ሌሎች ሲናገሩ የማይረባ አስተያየት አትስጥ።

10 ከነጐድጓዱ በፊት ብልጭታው ቀድሞ እንደሚታይ፥ ከትሑት ሰው እንዲሁ ስጦታው ይቀድማል።

11 ቀደም ብለህ ውጣ፤ የመጨረሻው ሰው አትሁን፥ ወዲያ ወዲህ ሳትል ወደ ቤትህም ሩጥ።

12 ራስህን አዝናና፤ ያሻህንም አድርግ፤ ግትር በመሆን ግን በኃጢአት አትውደቅ።

13 ስጦታዎች የለገሠህ፥ ይህን ሁሉ ያደረገልህን ፈጣሪ አመስግን።


እግዚአብሔርን መፍራት

14 እግዚአብሔርን የሚፈራ ሁሉ እርምቱን ይቀበላል፤ እርሱን የሚሹ ሁሉ ጸጋውን ያገኛሉ።

15 ሕጉን የሚከተል ሁሉ በእርሱ ይበለጽጋል፤ ለግብዞች ግን መሰናክል ነው።

16 እግዚአብሔርን የሚፈሩ የእርሱን ቸርነት ያገኛሉ፤ መልካም ሥራቸውም እንደ ብርሃን ያበራል።

17 ኃጢአተኛ ተግሣጽን አይቀበልም፤ ለፈጸመውም በደል ምክንያት አያጣም።

18 አስተዋይ ሰው የሚነግሩትን ይሰማል፤ መጻተኞችና ትዕቢተኞች ፍርሃትን አያውቁም።

19 ሳታስብ አታድርግ፤ በሠራኸውም አትጸጸትም።

20 በመጥፎ መንገድ አትጓዝ፥ በድንጋይ ላይ ልትወድቅ ትችላለህና።

21 በተስተካከለውም መንገድ አትተማመን፤

22 ከልጆችህም ተጠንቀቅ፤

23 በምታደርገው ነገር ሁሉ ራስህን ጠብቅ፤ ትእዛዛቱንም የምታከብርበት መንገድ ይኸው ነው።

24 በሕጉ የሚያምን ደምቦቹን ያከብራል፤ እግዚአብሔርን የማያምን ሁሉ ከቶውንም ከጉዳት አይወድቅም።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች