Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 መልካም ሚስት ያለው ባል እንደምን የተባረከ ነው፤ ዕድሜውም በእጥፍ ይረዝማል።

2 ጥሩ ሚስት ለባልዋ ደስታ ናት፤ ሕይወቱም ሰላም የሰፈነባት ትሆናለች።

3 መልካም ሚስት እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ከተተው ድርሻዎች፤ ከሁሉም የላቀችው ናት።

4 ሃብታም ሆኑ ድሀ፥ ልቦቻቸው በደስታ ይሞላሉ፤ በማንኛውም ወቅት ፊቶቻቸው የብርሃን ጸዳል ይለብሳሉ።

5 ሦስት የሚያስደነግጡኝ ነገሮች አሉ፤ አራተኛውም ያስፈራኛል፤ በመላው ከተማ የሚነገር ሐሜት፤ የሕዝብ ሁከተትና የሐሰት ክስ፥ ከሞት የከፋ አስደንጋጭ ድርጊቶች ናቸው።

6 በሴት የምትቀና ሴት ግን የልብ ቁስል ናት፤ ይህም የምላስ መቅሰፍት ነው።

7 ክፉ ሚስት በትክክል እንደማይገጥም ቀምበር ናት፤ እርሷን ለመግራት መሞከር ጊንጥ እንደ መያዝ ነው።

8 ጠጪ ሚስት እጅግ ታስቆጣለች፥ ውርደቷን ልትደብቅም አትችልም።

9 የሴት ዘማዊነት በድፍረቷ ይታወቃል፤ ቅንድቧም ይመሰክርባታል።

10 ከደፋሯ ሴት ልጅህን በሚገባ ጠብቅ፤ ካልሆነ ግን ምንም ከማድረግ አትመለስም።

11 ኀፍረት የማያውቁ ዐይኖቿን ተከታተል፤ ብታዋርድህ አይድነቅህ።

12 ጥም እንዳቃጠለው መንገደኛ አፏን ትከፍታለች፤ የገኘችውንም ውሃ ትጠጣለች፤ በየድንኳኑ ፊት ለፊት ትቀመጣለች፤ ለመጣው ፍላጻም ሰገባዋን ትከፍታለች።

13 የሚስት ሞገስ ባልዋን ያስደስታል፤ አያያዟም ኃይልን ይሰጠዋል።

14 ረጋ ያለች ሚስት የእግዚአብሔር ስጦታ ናት፤ መልካም አስተዳደግ በዋጋ አይተመንም።

15 ትሑት ሚስት እጥፍ ትርፍ ናት፤ ከንጹሕ ባሕርይ በላይ የሚወደድ የለም።

16 በእግዚአብሔር ተራሮች ላይ እንደምታብራው ፀሐይ ሁሉ፥ በጥሩ ቤት ውስጥ ያለ የመልካም ሴት ውበት እንዲሁ ነው።

17 በመልካም ቁመና ላይ የሚታይ ቁንጅና፥ በተቀደሰ መቅረዝ ላይ እንደሚያበራ ፋኖስ ነው።

18 ቀጥ ባሉ ተረከዞች ላይ የተሰኩ ውብ ባቶች፥ በብር መሠረት ላይ እንደተተከሉ የወርቅ ምሰሶዎች ናቸው።


አሳዛኝ ነገሮች

28 ልቤን የማያሳዝኑት ሁለት ነገሮች አሉ፤ ሦስተኛው ደግሞ ያስቆጣኛል። በድኀነቱ የተነሣ ወድቆ የሚቀር ጀግና፥ በጥላቻ ዐይን የሚታይ ጠቢብ፥ ከደግነት ወደ ኃጢአት ፊቱን የመሰለ ሰው፥ እግዚአብሔር ለአሰቃቂ ሞት መርጦታል።


ንግድ

29 ነጋዴ ከስሕተት፥ አትራፊ ከኃጢአት ይነጻል ለማለት እጅጉን ይከብዳል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች