Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


ምሳሌዎች

1 ነፍሴ የምትደሰትባቸው ሦስት ነገሮች አሉ፤ በእግዚአብሔርና በሰዎችም ዘንድ ደስታን ይፈጥራሉ። እነርሱም የወንድማማቾች ስምምነት፥ የጐረቤት መዋደድና፥ የሚግባቡ ባልና ሚስት ናቸው።

2 ነፍሴ የምትጠላቸው ሦስት ዓይነት ሰዎች አሉ። ህልውናቸውም ያንገበግበኛል። እርሱም ትዕቢተኛ ድኃ፥ ውሸታም ሀብታምና፥ ሐፍረተ-ቢስ ዘማዊ ሽማግሌ ናቸው።


ሽማግሌዎች

3 በወጣትነትህ ምንም ካልያዝህ በሽምግልና ዕድሜህ ምን ታገኛለህ?

4 ከነጭ ጠጉር ትክክለኛ ፍርድ፥ ከሽበት ጺም መልካም ምክር ሲገኝ ምንኛ እንደምን ያስደስታል!

5 ከሽማግሌዎች ጥበብ፥ ከታላላቅ ሰዎች ዘንድ ምክር ሲገኝ እንደምን ያስደስታል!

6 የሽማግሌዎች አክሊል በሳል ተሞክሮ፥ ክብራቸውም እግዚአብሔርን መፍራት ነው።


አኃዛዊ ምሳሌዎች

7 ደስተኞች ናቸው ብዬ የማስባቸው ዘጠኝ ሰዎች አሉ፤ አሥረኛው ምላሴ ላይ ነው፥ በልጆቹ የሚኮራ፥ የጠላቶቹን ውድቀት በዓይኑ የሚያይ፥

8 መልካም ሚስት ያለችው፥ ከበሬና ከአህያ ጋር የማይደክም፥ በምላሱ ክፉ ያልተናገረ፥ ከርሱ ላነሱ ሰው ያላደረ፥ የታደለ ነው።

9 ብልህነትን ያገኘ፥ ለሚናገረው አድማጭ የማያጣ ደስተኛ ነው።

10 ጥበብን የቀሰመ ታላቅ ነው፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ግን ከሁሉም የላቀ ነው።

11 እግዚአብሔርን መፍራት ከሁሉም በላይ ነው፥ ይህን ጥበብ ከተካነው ሰው ጋር ሊስተካከል የሚችል ይኖራልን?


ሴቶች

13 ከማንኛውም ዓይነት ቁስል ይልቅ የልብ ቁስል የከፋ ነው። ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ይልቅ የሴት ክፋት አስፈሪ ነው።

14 ጠላትህ ከሚያደርስብህ ሰቆቃ የከፋ ሰቆቃ አይኖርም። ከጠላትህ በቀል የከፋ በቀል አይኖርም።

15 ከእባብ መርዝ የባሰ መርዝ የለም፤ ከጠላትህ ቁጣ የከፋ ቁጣ አይኖርም።

16 ከክፉ ሴት ጋር ከመኖር፥ ከአንበሳ ወይም ከዘንዶ ጋር መኖርን እመርጣለሁ።

17 የሴት ጥላቻ ፊትዋን ይለውጠዋል፤ እንደ ድብም ያከስለዋል።

18 ባሏ ከጐረቤቶቹ ጋር ከእራት ሲወጣ፤ ሳይወድ በኀዘን ያቃስታል።

19 የሴትን ጥላቻ የሚያህል ከቶ ምንም የለም፤ የኃጢአተኛው ዕጣ ይውደቅባት፤

20 ጨቅጫቃ ሚስት ያለው ጨዋ ወንድ፤ በአሸዋ ጉብታ ላይ እንደሚራመድ ሽማግሌ ነው።

21 በሴት ልጅ ውበት አትማረክ፤ ስለ እርሷም ራስህን አትሳት።

22 ባል በሚስቱ ላይ ጥገኛ በሆነበት ቤት፤ መጥፎ ባሕርይ፥ ውርደትና ኀፍረት ይነግሣሉ።

23 ተስፋ መቁረጥ፤ የትካዜ መልክ፥ የልብ ስብራት፥ ይህ ሁሉ የክፉ ሚስት ውጤት ነው። የደከመ፥ እጅ የላመ ጉልበት፥ ባሏን ከምታሳዝን ሴት የሚገኝ በረከት ነው።

24 ኃጢአት በሴት ተጀመረ፤ ዕድሜ ለእርሷ ሁላችን እንሞታለን።

25 ለውሃ ቀዳዳ እንደማይተው፥ ለክፉ ሴትም ምላስ እንዲሁ ልጓም ያሻዋል።

26 አንተ የምትላት ካልፈጸመች፥ ከቤትህ ትውጣ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች