Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጠጪ ሠራተኛ አይበለጽግም፤ ትናንሾቹን ጉዳዮች የሚያቀል ቀስ በቀስ ይሰምጣል።

2 ወይን ጠጅና ሴቶች ዓዋቂዎችን ከስሕተት ይጥላሉ፤ ሴተኛ አዳሪዎችን የሚያዘወትር፥ ብሎ ብሎ አፍረተ ቢስ ይሆናል።

3 አፍረተ ቢሱ ውርስነቱ ለትሎች ነው፤ ሕይወቱንም ያጣል።


ከልቅ ንግግር ስለመታቀብ

4 ለማመን የሚቀድም ማስተዋል ይጐለዋል፤ ኃጢአት ኃጢአተኛን ይጎዳል።

5 በክፉ ነገር የሚደሰት ይኰነናል፤

6 ወሬን የሚጠላ ክፉን ያርቃል፤

7 የተነገረህን ፈጽሞ አትድገም፤ ከአደጋም ትጠበቃለህ።

8 ለወዳጅም ሆነ ለጠላት ስላደረግኸው አትንገር፤ አለመንገርህ ኃጢአት ካልሆነ በቀር አትግለጸው።

9 ብትናገር ይሰማብሃል፥ እንዲያ ከሆነ ደግሞ መታመንን ታጣለህ፤ ከጊዜም ብዛት ጥላቻን ታተርፋለህ።

10 አንድ ምሥጢር ሰምተሃልን? ከአንተው ጋር ይቀበር፤ ድፍረት ይኑርህ፥ አያፈነዳህም።

11 ሞኝ ሰው ስለ ሰማት ወሬ ይጨነቃል፤ በወሊድ ላይ እንዳለች ሴትም ያምጣል።

12 በሞኝ ዘንድ የታወቀ ወሬ፥ በጭን ላይ እንደተሰካ ፍላጻ ነው።


የሰማኸውን ሁሉ አትመን

13 ወዳጅህን ጠይቀው፥ ምናልባት ምንም አላደረገም ይሆናል፤ ካደረገም ዳግመኛ አያደርገውም።

14 ባልንጀራህን ጠይቀው፥ ምናልባት ያለው ነገር አይኖርም ይሆናል፤ ተናግሮም ከሆነ አይደግመውም።

15 ወዳድህን ጠይቀው፥ ሐሜት የተለመደ ነውና የሰማኸውን ሁሉ አትመን።

16 አንዳንድ ሰው ክፉ ነገር ሳያስብ ያዳልጠዋል፤ ከቶስ በንግግሩ ያልበደለ ይኖራልን?

17 ከማስፈራራትህ በፊት ባልንጀራህን ጠይቅ፤ የልዑል እግዚአብሔርን ሕግ ታዘዝ።


ትክክለኛና የተሳሳተ ጥበብ

20 ጥበብ ማለት ጌታን መፍራት ነው፤ መሠረቱም ሕጉን መፈጸም ነው።

22 በክፋት መካን ግን ጥበብ አይደለም፤ የኃጢአተኞች ምክር ጥንቃቄ የጎደለው ነው።

23 ጣዕም ያጣ ብልጥነት አለበት፥ ጥበብ የሌለው ሁሉ ሞኝ ነው።

24 በብልጥነት ሕጉን ከመጣስ፥ በፍርሃት ለእርሱ አድሮ አላዋቂ መሆን ይቀላል።

25 እንከን የማይወጣለት፥ ነገር ግን ታማኝነት የጐደለው ኃጢአት አለ። በሌሎች የዋህነት በመጠቀምም የሚያተርፉ አሉ።

26 ኀዘን እንደከበደው ሁሉ ጐብጦ የሚሄድ ሰው አለ፥ በውስጡ ግን ከማታለል በቀር ምንም የለም።

27 ፊቱን ይሸሽጋል፤ ያልሰማም ይመስላል፤ ካልተጋለጠ በቀር ባንተ ላይ ይሠራብሀል።

28 ኃይል በማጣቱም ብቻ ከመበደል የሚታቀብ አለ፤ አጋጣሚውን ካገኘ ግን ወደ ኋላ አይልም።

29 ሰውን በመልኩ መለየት ይቻላል፤ ተመራማሪ ደግሞ በፊቱ ገጽታ ይታወቀል።

30 ሰው በአለባበሱ፥ በአሳሳቁ፥ በአነጋገሩ ይለያል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች