ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ጌታ ሰውን ከመሬት ፈጠረ፤ ወደ እርሷም ይመልሰዋል። 2 ለሰዎች ብዙ ቀናትንና ጊዜም ሰጣቸው፤ በምድርም በሚገኘው ላይ ሁሉ ሥልጣንን ሰጣቸው። 3 እንደ ራሱ ብርታትን አለበሳቸው፤ በአምሳሉ ፈጠራቸው። 4 የዱር አውሬዎችና ወፎች እንዲታዘዟቸው፥ የምድር ፍጥረት ሁሉ እንዲፈራቸው አደረገ። 6 ምላስን፥ ዓይንና ጆሮን ሠራላቸው፤ የሚያስቡበትንም ልቦና ሰጣቸው። 7 በዕውቀትና በማስተዋል ሞላቸው፤ ደግንና ክፉን እንዲለዩ አደረጋቸው። 8 የሥራዋቹንም ታላቅነት እንዲያዩ፥ በልባቸውም የራሱን ብርሃን አኖረ። 9 ስለ ድንቅ ሥራዎቹ እንዲገሩ፥ 10 ቅዱሱን ስሙን እንዲያመሰግኑ፥ 11 ዕውቀትንም በፊታቸው አኖረ፥ የሕይወትንም ሕግ ሰጥቷቸዋል። 12 ከነሱ ጋር ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ገብቷል፤ ፍርዶቹንም ገልጾላቸዋል። 13 ዐይኖቻቸው የክብሩን ታላቅነት አይተዋል፤ ጆዎቻቸው የድምፁን ግርማ ሰምተዋል። 14 “ከክፉ ሁሉ ተጠንቀቁ” አላቸው፥ እያንዳንዳቸው ባልንጀሮቻቸውን በተመለከተም ትዕዛዝ ሰጥቷቸዋል። መለኮታዊው ዳኛ 15 መንገዶቻቸው ከእይታው አያመልጡም፤ በዐይኑም ይከታተላቸዋል። 17 በእያንዳንዱ ሀገር አስቀምጧል፥ ይሁን እንጂ እስራኤል የእግዚአብሔር ድርሻ ናት። 19 ሥራዎቻቸው ሁሉ በሱ ፊት እንደ ፀሐይ ግልጽ ናቸው፤ ዐይኖቹ ሁልጊዜ በባሕሪያቸው ላይ ያነጣጥራሉ። 20 ክፋታቸው ከእርሱ አይሰወርም፤ ኃጢአቶቻቸውም በፊቱ ይቀርባሉ። 22 ምጽዋት ለእርሱ እንደ ቀለበት ማኀተም ነው፤ በሰው ውስጥ ያለው ደግነት ለልክ እንደ ዐይን ብሌን ያስደስተዋል፤ 23 አንድ ቀን ተነሥቶ ይሸልማቸዋል፤ ዋጋቸውን ለየራሳቸው ይከፍላቸዋል። 24 ነገር ግን ንስሐ ለሚገቡ እንዲመለሱ ይፈቀድላቸዋል፤ ተስፋ የቆረጡትንም ያበረታቸዋል። የንስሐ ጥሪ 25 ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፥ ኃጢአቶችህንም አውግዝ፥ በፊቱ ለምን፥ እሱንም አታስቀይመው። 26 ወደ ልዑል እግዚአብሔር ተመለስ፤ ከክፉ ነገር ራቅ፤ መጥፎውን ሁሉ ጥላ። 27 በሕይወት እያለን ከፍ ከፍ ካላደረግነው፥ ሲኦል ወርዶ የሚያመሰግነው ይኖራልን? 28 የሞቱትን እንደ ሌሎች ሁሉ ማመስገን አይችሉም፤ እግዚአብሔርን የሚያወድሱ ሕያዋንና ጤነኞች ብቻ ናቸው። 29 የእግዚአብሔር ምሕረት ምንኛ ታላቅ ነው፤ ወደሱ ለሚመለሱ ሰዎች ይቅርታው ምንኛ የበዛ ነው። 30 የምንሻው ሁሉ ሊኖረን አይችልም፤ ሰዎች ዘላለማዊ አይደለንምና። 31 ከፀሐይ የበለጠ ድምቀት ያለው አለን? እንዲያም ሆኖ ግን ይደበዝዛል፥ ሥጋና ደምም ከክፋት በስተቀር የሚያልሙት የለም። 32 አምላክ የሰማይ ሠራዊትን ይቆጣጠራል፥ እኛ ግን ትቢያና አመድ ብቻ ነን። |