Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


የግትሮች ዕጣ

1 የማይረቡ ብዙ ልጆች አትመኝ፤ በክፉ ልጆች አትደሰት።

2 ምንም ያህል ቢበዙ ፈሪሃ እግዚአብሔር ካላደረባቸው ያብራክህ ክፋዮች በመሆናቸው ብቻ አትደሰት።

3 ረጅም ዕድሜ ይኖራቸዋል ብለህ አትጠብቅ፤ በቁጥራቸውም ብዛት እምነት አይኑርህ፤ ከሺህ አንድ የተሻለ ይመረጣል፤ ክፉዎች ከመውለድ ያለ ዘር ማለፍ ይቀላል።

4 አንድ አስተዋይ ከተማዋን በሰው ይሞላታል፤ የሕገ ወጥ ሕዝቦች ዘር ግን ይደመሰሳል።

5 ይህን የመሰሉ ሁናቴዎች ዐይኖቼ አይተዋል፤ በጣም የሚገርሙ ነገሮችን ጆሮዎቼ ሰምተዋል።

6 በኃጢአተኞች ማኀበር እሳት ይንቀለቀላል፥ በማይታዘዝ ሕዝብ ላይ ቁጣ ይነዳል።

7 ጥንታውያኑን ግዙፎች እግዚአብሔር ይቅርታ አላደረገላቸውም፤ በኃይላቸውም ተኩራርተው በእርሱ ላይ አምፀዋልና።

8 ከሎጥ ጋር የሚኖሩትን ሰዎች አልሳሳላቸውም፤ በትዕቢታቸው ምክንያት ጠላቸው።

9 በኃጢአታቸው የተኩራሩ የጥፋት ሕዝቦችን አልራራላቸውም፤

10 በልበ ደንዳናነታቸው በአንድ ላይ የተሰበሰቡትን ስድስት መቶ ሺህ እግረኛ ተጓዦችን እንኳ አላዘነላቸውም።

11 የቀረው ግትር ሰው አንድ ሆኖ፥ እርሱም ሳይቀር አምልጦ ቢሆን ኖሮ፥ የሚያስደንቅ ይሆን ነበር። ምሕረትና ቁጣ የእግዚአብሔር ናቸው፤ ይቅርታ ሊያደርግ ወይም ሊጠፋ ሥልጣን ያለው እርሱ ብቻ ነው።

12 ምሕረቱ ታላቅ እንደሆነ ሁሉ፥ ኃያልነቱ አስፈሪ ነው። ሰዎችን እንደ ሥራቸው ይፈርዳል።

13 ኃጢአተኛ በተንኮል ካገኘው ጥቅም ጋር አያመልጥም፤ የጻድቁም ትዕግሥት ያለ ዋጋ አይቀርም።

14 መልካም ሥራን ሁሉ ይመለከታል፤ እያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው ዋጋውን ያገኛል።


የቅጣት አይቀሬነት

17 “ከእግዚአብሔር እሸሸጋለሁ፥ እዚያ ላይ ሆኖ ማን ያስታውሰኛል፤ ከብዙ ሰው መካከል እኔ አልለይም፤ በፍጥረትስ ዐይን ኢምንት አይደለሁምን?” አትበል

18 ሰማይ፥ ከሰማይም በላይ ያሉ ሰማያት፥ መሬትና እልም ያለ ጥልቀትም እርሱ በመጣ ጊዜ እንደሚንቀጠቀጡ ተመልከት።

19 ተራሮችና የምድር መሠረቶች እሱ ሲመለከታቸው በፍርሃት ይርዳሉ።

20 ግን ይህን ሁሉ ሰዎች አያስቡትም፤ የሱን መንገዶች በጥንቃቄ የሚያስተውላቸው ማን አለ?

21 ማንም ሊያየው እንደማይችለው የነፋስ ማዕበል፤ አብዛኛዎቹ ሥራዎቹ ድብቅ ናቸው።

22 የጽድቅ ሥራዎቹን ማን ያበሥራል? ማንስ ይጠብቃቸዋል? የተስፋው ቃል በጣም ሩቅ ነው።

23 ደካማ አስተሳሰቦች ያለው ሰው፥ የማይረባ፥ ከትክክለኛው መንገድ የወጣ፥ በመሳሳቱ የማይቆጭ ሰው አመለካከት ይህን ይመስላል።


ሰዎች በፍጥረት ዓለም

24 ልጄ ሆይ አድምጠኝ፥ ዕውቀትንም አግኝ፥ ልብህን በቃሎቼ ላይ አድርግ።

25 ሥርዓትን በዘዴ፥ እውቀትንም በትክክል አሳይሃለሁ።

26 ጌታ በመጀመሪያ ሥራዎቹን በፈጠረ ጊዜ፥ ለሁሉም ቦታቸውን ሰጥቷቸዋል።

27 ሥራዎቹን ለሁልጊዜ፥ ከመነሻ እስከ መጨረሻ ሐረጋቸው ድረስ ወስኗል፤ ረኃብና ድካም አያውቁም፤ ተግባራቸውንም አይዘነጉም።

28 አንዱ በሌላው ሕይወት ከቶውንም ገብቶ አያውቅም፤ የፈጣሪውን ቃል የማይፈጽም የለም።

29 ከዚህ በኋላ ጌታ ወደ ምድር ተመለከተ፤ ምድርን በመልካም ሥራው ሞላት።

30 የምድርን ገጽ በሁሉም ዓይነት እንስሳት ሸፈናት፤ ሁሉም ወደ እርሷው ይመለሳሉ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች