Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 114 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሃሌ ሉያ! እስራኤል ከግብጽ፥ የያዕቆብም ቤት ከእንግዳ ሕዝብ በወጣ ጊዜ፥

2 ይሁዳ መቅደሱ፥ እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።

3 ባሕር አየች፥ ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።

4 ተራሮች እንደ አውራ በጎች፥ ኮረብቶችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ።

5 አንቺ ባሕር የሸሸሽው፥ አንቺስ ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽው፥ ምን ሆናችሁ ነው?

6 እናንተም ተራሮች፥ እንደ አውራ በጎች፥ ኮረብቶችስ፥ እንደ ጠቦቶች ለምን ዘለላችሁ?

7 በያዕቆብ አምላክ ፊት፥ በጌታ ፊት ምድር ተናወጠች፥

8 ዐለቱን ወደ ውኃ መቆሚያ፥ ድንጋዩንም ወደ ውኃ ምንጭ ይለውጣል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች