Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ዮዲት 1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


1 የሆሎፎርኒስ ዘመቻ ናቡከደነፆርና አርፋስክድ

1 በታላቂቱ ከተማ በነነዌ በአሦራውያን ላይ የገዛው ናቡከደነፆር ከነገሠ ዐሥራ ሁለተኛው ዓመት ነበር፤ በዚያን ጊዜ አርፋክስድ በኤቅባጥና ባሉ በሜዶናውያን ላይ ነግሦ ነበር።

2 በኤቅባጥና ከተማ ዙሪያ ስፋታቸው ሦስት ክንድ፥ ቁመታቸው ስድስት ክንድ የሆኑ በተጠረበ ድንጋይ ቅጥሮችን ገነባ። የቅጥሮቹ ቁመት ሰባ ክንድ፥ ስፋቱ ሃምሳ ክንድ አድርጎ ሠራ።

3 በየበሮች ቁመታቸው መቶ ክንድ፥ የመሠረታቸው ስፋት ስለሳ ክንድ የሆኑ ግንቦች አቁሞ ነበር።

4 የበራፎቹ ቁመት ወደ ላይ ሰባ ክንድ ጐናቸው አርባ ክንድ ሆኖ የእግረኛ ጦር ወታደሮች በሰልፍ እንዲወጡባቸው ሆነው የተሠሩ ነበሩ።

5 በእነዚያ ቀኖች ንጉሥ ናቡከደነፆር በሰፊ ሜዳ በንጉሥ አርፋክስድ ላይ ጦርነት ከፈተ፥ ያም በራጋው አውራጃ ያለ ሜዳ ነው።

6 በአምባው የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ፥ በኤፈራጥስ፥ በጤግራን፥ በሄዳስጴን ያሉ ሁሉ፥ በኤለሜዖን ንጉሥ በአርዮክ ግዛት ያሉ ሁሉ ከናቡከደነፆር ጋር ወገኑ፥ ብዙ ሕዝቦችም የካሉድን ልጆች ለመውጋት ተሰበሰቡ።

7 ከዚህ በኋላ የአሦር ንጉሥ ናቡከደነፆር በፋርስ ለሚኖሩ ሁሉ፥ በምዕራብ ለሚኖሩ ሁሉ፥ በኪልቅያና በደማስቆ፥ በሊባኖስና በአንቲሊባኖስ ለሚኖሩ ሁሉ፥ በባሕር ጠረፍ ለሚገኙ ሁሉ ላከ፥

8 በቀርሜሎስና በገለዓድ ሕዝቦች መካከል ላሉ፥ በላይኛው ገሊላና በሰፊው በኤስድራሎን ሜዳ ለሚኖሩ ሁሉ፥

9 በሰማርያና በከተሞችዋ ላሉ ሁሉ፥ በዮርዳኖስ ማዶ እስከ ኢየሩሳሌም፥ ባታኒ፥ ኬሎስ፥ ቃዴስ፥ የግብጽ ወንዝ፥ ታፍናስ፥ ራምሴና ጌሴም ምድር ሁሉ፥

10 እስከ ጣኒስና ሜምፊስ በላይ፥ በግብጽ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ድረስ ለሚኖሩ ሁሉ ላከ።

11 ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ የአሦርን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቃል ንቀው ከእሱ ጋር በጦርነት ላይ ለመሰለፍ እንቢ አሉ፤ አልፈሩትምና፥ እንደ አንድ ሰው ቆጥረዉታልና፤ መልክተኞቹንም ባዶ እጃቸውንና አዋርደው ከፊታቸው መለሱአቸው።

12 ናቡከደነዖር በምድሪቱ ሁሉ ላይ እጅግ ተቆጣ፥ የኪልቅያን፥ የደማስቆን፥ የሶርያን አገሮች እንደሚበቀል፥ በሞዓብን ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፥ የአሞንን ልጆች፥ ይሁዳን በሙሉ፥ እስከ ሁለት ባሕሮች ጠረፍ ድረስ በግብጽ የሚኖሩትንም ሁሉ በሰይፍ እንደሚገድል በዙፋኑና በመንግሥቱ ማለ።


አርፋክስድ እንደ ተሸነፈ

13 በዓሥራ ሰባተኛው ዓመት ሠራዊቱን በንጉሥ አርፋክስድ ላይ አሰለፈ፥ በጦርነቱም አሸነፈ፥ የአርፋክስድን ሠራዊቱን ሁሉ፥ ፈረሰኞቹንና ሠረገላዎቹን ገለበጠ።

14 በከተሞቹም ላይ ጌታ ሆነ፥ እስከ ኤቅባጥናም ደረሰ፥ ግንቦቹን ያዘ፥ አደባባዮቸን በረበረ፥ ክብርዋንም በውርደት ቀየረው።

15 አርፋክስድንም በራግው ተራሮች ላይ ያዘውና በጦር ወጋው፥ እስከዚህችም ቀን ድረስ አጠፋው።

16 ከዚህ በኋላ ከመላ ሠራዊቱና ከብዙ ጦረኞቹ ጋር ተመለሰ፤ በዚያም እርሱና ሠራዊቱ ሁሉ እየበሉና እየጠጡ መቶ ሃያ ቀን ተቀመጡ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች