Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

1ኛ መጽሐፈ መቃብያን 15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


ሰባተኛው የአንጦዮኩስ ደብዳቤ እና የዶላ መያዝ

1 የንጉሥ ዲሜጥሮስ ልጅ አንጥዮኩስ ከሜዲትሪንያን ባሕር አካባቢ ሆኖ ካህንና የአይሁዳውያን ሹም ለሆነው ለስምዖንና ለሕዝቡም ሁሉ ደብዳቤ ላከ፤

2 ደብደቤው የሚለው እንዲህ ነበር፥ “ንጉሥ አንጥዮኩስ ለሊቀ ካህናትና ለሕዝብ መሪ ስምዖንና ለአይሁድ ሕዝብም ሰላምታ ያቀርባል።

3 ክፉ ሰዎች የአባቶቻችንን መንግሥት ስለያዙብኝ ይህን መንግሥት ልክ እንደ ቀድሞው ሆኖ እንዲመለስ ለማድረግ አስቤአለሁ፤ ስለዚህ ብዙ ወታደሮች ሰብስቤአለሁ፤ የጦር መርከቦችም አዘጋጅቻለሁ፤

4 ይህን ያደረግሁት ወደ እዚያ አገር ለመሻገር፥ አገራችንን የጠፉትንና የመንግሥቴ ከተሞች የደመሰሱትን ሰዎች ለመበቀል ነው።

5 አሁንም ቢሆን ከእኔ በፊት የነበሩት ነገሥታት የተውልህን ግብርና ሌሎችንም የተውልህን ስጦታዎች ሁሉ እተውልሀለሁ።

6 በአገርህ የሚያገለግለውን ገንዘብ አትመህ እንድታወጣ መብት ሰጥቼሃለሁ፤

7 ኢየሩሳሌምና ቤተ መቅደሱ ነጻ ናቸው፤ የሠራሃቸው የጦር መሣሪያዎች ሁሉ፥ ያነጽኻቸው ምሽጐች ያንተ ሆነው ይቀራሉ፤

8 የአሁኑም ሆነ የወደፊቱ ለመንግሥት ግምጃ ቤት ገቢ መሆን የሚገባቸው ዕዳዎች ሁሉ ከዛሬ ጀምሮ ለዘወትር ተትተውልሃል።

9 መንግሥታችንን ከያዝን በኋላ ለአንተም ሆነ ለሕዝብህ፥ ለቤተ መቅደሱም ምስጋናችሁ ለመላው ዓለም ግልጽ የሚሆንበት ክብር ይሰጣችኋል”።

10 በመቶ ሰባ አራት (139) ዓመተ ዓለም አንጥዮኩስ ወደ አባቶቹ አገር ሄደ፤ ወታደሮች ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ከትሪፎን ጋር ጥቂት ሰዎች ብቻ ቀሩ።

11 አንጥዮኩስ እየተከታተለ ትሪፎንን አባረረው፤ እርሱም በባሕር አጠገብ ወዳለችው ወደ ዶራ ሽሽቶ ሄደ፤

12 ምክንያቱም መካሪዎች እንደተመካከሩበትና ወታደሮችም እንደነገዱበት ስለተገነዘበ ነው።

13 አንጥዮኩስ ከአንድ መቶ ሃያ ሺህ እግረኛ ጦረኞችና ከስምንት ሺህ ፈረሰኛ ጦረኞች ጋር ወደ ዶራ ሂዶ ሠፈረ።

14 ከተማዋን ከበባት፤ መርከቦች በፊትዋ ተሰበሰቡ። ከተማዋም በምድርም፥ በባሕርም ስለተጠቃች ማንም መግባት ወይም መውጣት አይችልም ነበር። መልዕክተኞቹ ከሮም ወደ ይሁዳ ተመለሱ፤ ከሮም ጋር ያለው ግንኙነት ይፋ ተደረገ

15 ኑመንዩስና ጓደኞቹ ለነገሥታትና ለሀገሮች የተጻፉትን ደብዳቤዎች ይዘው ከሮም ተመለሱ፤ የደብዳቤዎቹም ቃል እንዲህ የሚል ነው፤

16 “የሮማውያን ቆንሲል ሉስዮስ ለንጉሥ ጰጠሎማዎስ ሰላምታ ያቀርባል።

17 ከሊቀ ካህናት ስምዖንና ከአይሁድ ሕዝብ የተላኩ መልእክተኞች የቀድሞውን ወዳጅነትና ቃል ኪዳን ለማደስ እንደ ወዳጆችና እንደ ጦር ጓደኞች ወደ እኛ መጡ፤

18 አንድ ሺህ ምናን የሚመዝን የወርቅ ጋሻ አመጡልን።

19 ስለዚህ በክፉ ነገር እንዳይፈልጓቸው እነሱንም ሆነ ከተሞቻቸውን ወይም አገራቸውን እንዳይወጉ፥ እነርሱን ከሚይጓቸው ሰዎች ጋር እንዳይስማሙ ለነገሥታትና ለሀገሮች መጻፍ ወስነናል።

20 ከእነርሱ የተላከልንንም ጋሻ ለመቀበል ወስነናል።

21 ክፉ አደራጊዎች ከእነርሱ አገር ሸሽተው ወደ እናንተ ቢመጡ በሕጋቸው መሠረት እንዲቀጣቸው ለሊቀ ካህናት ስምዖን አሳልፋችሁ ስጧቸው”።

22 ይህ ዓይነት ደብዳቤ ለዲሜጥርስና ለአጣሉስ፥ ለአርያራትና ለአርሳቂም ተጻፈ።

23 እንዲሁም ለሀገሮች ሁሉ፥ ለሳምጳላሚ፥ ለጸሎስ፥ ለሚንጸስ፥ ለሊስዮን፥ ሊቃሪያ፥ ለሳሞስ፥ ለጹንፍልያ፥ ለሲቅያ፥ ለህሊቃርናስ፥ ለሮድስ፥ ለፋሊሌዳ፥ ለቆስ፥ ለሲደን፥ ለአራደን፥ ለጐሪቲና፥ ለቅኒዶስ፥ ለቆጱሮስ፥ ለቄራኔ፥ ተጻፈ።

24 የደብዳቤዎቹ ግልባጭ ለሊቀ ካህናቱ ለስምዖን ተጽፎ ተሰጠው።


ሰባተኛው አንጥዮኩስ ዳራን ለመክበብ ተዘጋጀ፤ በዚህም የተነሣ ግጭት በመነሣቱ ለስምዖን ወቀሳ ላከበት።

25 ንጉሥ አንጥዮኩስ ወታደሮች ወደ ዶራ ሳይቋርጡ እንዲጠጉ እያደረገና የጦር መዘውሮች እየሠራ በዶራ አጠገብ ሠፈረ፤ ትሪፎንን ዘግቶበት ስለ ነበር ማንም ሊገባ ወይም ሊወጣ አይችልም ነበር።

26 እንዲዋጉለት ሁለት ሺህ ምርጥ ሰዎች ስምዖን ላከበት፤ እንዲሁም ብርና ወርቅ፤ ለትጥቅ የሚያስፈልጉ ብዙ እቃዎች ላከለት።

27 አንጥዮኩስ ይህን መቀበል አልፈለገም፤ እንዲያውም ከዚህ ቀደም ከስምዖን ጋር ያደረገውን ውል ሁሉ አፈረሰ፤ ከዚህ ቀደም ከሰምዖን ጋር ያደረገውን ውል ሁሉ አፈረሰ፤ በስምዖንም ላይ ተለወጠበት።

28 ከስምዖን ጋር እንዲነጋገር አጤኖበየስን ወደ ስምዖን ላከው፤ ንግግሩም እንዲህ የሚል ነበር፥ “የመንግሥቴ ከተሞች የሆኑትን ኢዮጶን፥ ጌዘርን፥ የኢየሩሳሌምን ምሽግ ይዛችኋል፤

29 ምድሮቻቸውን አጥፍታችኋል፤ በሀገሩ ላይ ብዙ ክፉ ነገር አድርጋችኋል፤ የመንግሥቴን ብዙ ቦታቸውን ይዛችኋል፤

30 እንግዲህ አሁን የያዛችኋቸውን ከተሞች መልስ፤ ከይሁዳ ምድር ውጭ የሆኑትን የያዛችኋቸውን ቦታዎች ግብር ክፈል።

31 አለበለዚያ በእነርሡ ፈንታ አምስት መቶ የብር መክሊት ሰጡ፤ ከዚህም በላይ ደግሞ ስላደረሳችሁት ጥፋትና ጉዳት፥ ስለከተሞች ግብር አምስት መቶ የብር መክሊት ተጨማሪ ስጡ፤ አይሆንም ካላችሁ መጥተን እንዋጋለን”።

32 የንጉሡ ወዳጅ አጠኖብዮስ ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ የስምዖንን ታላቅነት፥ በወርቅና በብር የተሠራውን ሣጥን፥ ብዙ ጌጣጌጥንም አየና በጣም አቀነቀ፤ የንጉሡንም ቃለ ለስምዖን ነገረው።

33 ስምዖንም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እኛ የያዝነው ጠላቶች ለጥቂት ጊዜ በግፍ የወሰድብንን የአባቶቻችንን ርስት ነው እንጂ የሌላውን ምድር ወይም የሌላውን ሰው ንብረት አይደለም።

34 ምቹ ጊዜ አጋጥሞን ነው የአባቶቻችንን ርስት መመለስ የቻልነው።

35 መልሱልን ስለምትላቸው ኢዮጴና ጌዘር እንደሆነ እነዚህ ከተሞች በሕዝቡና በሀገራችን ላይ ብዙ ክፉ ነገር ያደረጉ ናቸው፤ ለነዚህ አንድ መቶ መክሊት እንሰጣለን።” አጠናብዩስ ምንም ቃል አልተነፈሰም።

36 በጣም ተቆጥቶ ወደ ንጉሡ ተመለሰ፤ ይህን ነገርና ያየውን የስምዖንን ክብር ለንጉሡ ነገረው፤ ንጉሡም እጅግ በጣም ተቆጣ።


የጠረፍ አስተዳዳር ከንደብዮስ ይሁዳን ወጋ

37 ትሪፎን በመርከብ ተሳፍሮ ወደ ኦርቶሲያ ሸሽቶ ሄደ።

38 ንጉሡ ከንደብዮስን የባሕሩ ጠረፍ አገር የጰራልያ የበላይ የጦር መሪ አድርጐ ሾመው፤

39 ሠፈሩን ከአይሁድ ፊት ለፊት እንዲያደርግ፤ ቄድሮንን እንደገነባ፤ መዝጊያዎችዋን እንዲያጠናክርና ሕዝቡንም እንዲወጋ አዘዘው፤ ንጉሡ ትሪፎንን ለመከታተል ገሠገሠ።

40 ከንደክዮስ ወደ ያምንያ ሂዶ ሕዝቡን ማስቆጣትና ወደ ይሁዳ አገር መግባት፤ መማረክና ሰዎችን መጨረስ ጀመረ፤

41 ቴድሮንን እንደገና ገነባት አነጻት፤ ንጉሡ አዞት እንደነበረው መውጫ ለማግኘትና የይሁዳን አገር መንገዶች ለመሰለል ፈረሰኛና እግረኛ ወታደሮችን እዚያ አስቀመጠ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች