ናሆም INTRO1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምመግቢያ ትንቢተ ናሆም ከጥንት ጀምሮ የእስራኤል ቀንደኛ ጠላት ስለ ነበረችው የአሦር ዋና ከተማ ስለ ነነዌ መደምሰስ የሚያበሥር ቅኔ ነው። ነነዌ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሰባተኛው ምእት ዓመት መጨረሻ ላይ መደምሰስዋ፥ እግዚአብሔር በጨካኝና በትዕቢተኛ ሕዝብ ላይ እንዴት እንደሚፈርድ ያሳያል። አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት 1. አስፈሪው የእግዚአብሔር ቊጣ 1፥1-6 2. በአሦር ላይ የተላለፈው ፍርድ ለእስራኤል ሕዝብ ተስፋ ማስገኘቱ 1፥7-15 3. የአሦር ዋና ከተማ ነነዌ መጥፋት 2፥1—3፥19 |