ሶፎንያስ 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ጠፍተዋልና፥ ብርም የተሸከሙ ሁሉ ተቈርጠዋልና አልቅሱ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 እናንተ በመክቴሽ ገበያ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤ ነጋዴዎቻችሁ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይሞታሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ አልቅሱ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ይጠፋሉና፥ ብርም የሚመዝኑ ሁሉ ይቆረጣሉና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 እናንተ ከከተማው በታችኛው ክፍል የምትኖሩ ሁሉ ነጋዴዎቻችሁ ስለሚወገዱና በብር የሚነግዱ ሁሉ ስለሚጠፉ ይህን ድምፅ በምትሰሙበት ጊዜ ‘ዋይ! ዋይ!’ እያላችሁ አልቅሱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ጠፍተዋልና፥ ብርም የተሸከሙ ሁሉ ተቈርጠዋልና አልቅሱ። ምዕራፉን ተመልከት |