Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘካርያስ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እኔም፦ አንተ ወዴት ትሄዳለህ? አልሁ። እርሱም፦ የኢየሩሳሌምን ወርድና ርዝመት ስንት መሆኑን ሰፍሬ አይ ዘንድ እሄዳለሁ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እኔም፣ “የት ልትሄድ ነው?” አልሁት። እርሱም፣ “የኢየሩሳሌም ርዝመትና ስፋት ምን ያህል እንደ ሆነ ለመለካት መሄዴ ነው፤” አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከዚያም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። እርሱም፦ “እነዚህ ይሁዳን፥ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበተኑ ቀንዶች ናቸው” ብሎ መለሰልኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እኔም “ወዴት እየሄድክ ነው?” ብዬ ጠየቅሁት፤ እርሱም “የኢየሩሳሌም ርዝመትና ስፋት ምን ያኽል እንደ ሆነ ለመለካት መሄዴ ነው” አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እኔም፦ አንተ ወዴት ትሄዳለህ? አልሁ። እርሱም፦ የኢየሩሳሌምን ወርድና ርዝመት ስንት መሆኑን ሰፍሬ አይ ዘንድ እሄዳለሁ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘካርያስ 2:2
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መጠ​ንዋ ወደ ጋሬብ ኮረ​ብታ በቀ​ጥታ ወደ ፊት ይሄ​ዳል፤ ወደ ጎዓ​ትም ይዞ​ራል።


ወደ​ዚ​ያም አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም መልኩ እን​ደ​ሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ናስ መልክ የመ​ሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፤ በእ​ጁም የተ​ልባ እግር ገመ​ድና የመ​ለ​ኪያ ዘንግ ነበረ፤ እር​ሱም በበሩ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።


“ለከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ይዞታ በተ​ቀ​ደ​ሰው የዕጣ ክፍል መባ አጠ​ገብ ወርዱ አም​ስት ሺህ፥ ርዝ​መ​ቱም ሃያ አም​ስት ሺህ የሆ​ነ​ውን ስፍራ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ። እር​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ይሆ​ናል።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ኢየሩሳሌም በምሕረት ተመልሻለሁ፣ ቤቴ ይሠራባታል፣ በኢየሩሳሌምም ላይ ገመድ ይዘረጋበታል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ከእኔም ጋር ይነጋገር የነበረውን መልአክ፦ እነዚህ የኢፍ መስፈሪያውን ወዴት ይወስዱታል? አልሁት።


አሁን ግን ወደ ላከኝ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ እንኳ፦ ‘ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ?’ ብሎ አይ​ጠ​ይ​ቀ​ኝም።


በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፤ እንዲህም ተባልሁ “ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች