ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጥበብ 10:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 በተበረታቱበትም ሰዎች ላይ ግዛትንና የመንግሥትን ሹመት እስከምታመጣለት ድረስ በታሠረበት አልተለየችውም። የናቁትንና ያነወሩትንም ሐሰታቸውን ገለጠችባቸው። የዘለዓለምንም ክብር ሰጠችው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ከጉድጓድ ውስጥ አብራው ገባች፤ በሰንሰለት በታሰረ ጊዜ አልተወችውም፤ በትረ መንግሥቱን እስኪጨብጥ፥ በጨቋኞችም ላይ ሥልጣንን እስኪያገኝ፥ ከጐኑ አልጠፋችም። በውሸት ያሙትን ሁሉ፥ ሐሰተኞች እንደ ሆኑ አግልጣለች፤ ዘላለማዊ ክብርንም አጐናጽፋዋለች። ምዕራፉን ተመልከት |