ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 9:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 በጧትም በአንድነት ገሥግሠው ሄዱ፤ ወደ ሰርጉም ደረሱ፤ ጦብያም ያን ብር ባመጣለት ጊዜ ሩፋኤልን መረቀው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 በማግስቱ ጧት በማለዳ ተነሥተው አብረው ወደ ሰርጉ ሄዱ። ወደ ራጉኤልም ቤት ሲገቡ ጦብያን በማዕድ ተቀምጦ አገኙት። ጦብያ በፍጥነት ተነሣና ጋባኤልን ሰላም አለው፤ ገባኤል እያለቀሰ እንዲህ ሲል ባረከው “አንተ ደግ ልጅ፥ የደጉ፥ የጻድቁና የለጋሱ ልጅ! ጌታ የሰማይን በረከት ለአንተና ለሚስትህ፥ ለሚስትህም አባትና እናት ይስጥ፤ የአጎቴን ልጅ የጦቢትን ሕያው አምሳል ያሳየኝ እግዝአብሔር የተባረከ ይሁን።” ምዕራፉን ተመልከት |