ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 7:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ወደ ራጉኤልም ቤት ደረሱ፤ ሣራም ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው፤ እንዲሁ እነርሱም እርሷን ደስ አሰኙአት፤ ወደ ቤትም አስገባቻቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ወደ ኤቅባጥና ከተማ በገቡ ጊዜ ጦብያ “ወንድሜ አዛርያ በቀጥታ ወደ ወንድማችን ወደ ራጉኤል ቤት ውሰደኝ” አለው። እሱም ወደ ራጉኤል ቤት ወስደው፤ ራጉኤልም በግቢው አጥር በር አጠገብ ተቀምጦ አገኙት፤ እነርሱ አስቀድመው ሰላምታ አቀረቡለት። እርሱም “እንደምናችሁ ወንድሞቼ፥ እንኳን ደኀና መጣችሁ” አለና ወደ ቤቱ አስገባቸው። ምዕራፉን ተመልከት |