ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 በየጊዜውም ፈጣሪህ እግዚአብሔርን አመስግነው፤ ጎዳናህም የቀና ይሆን ዘንድ ወደ እርሱ ጸልይ፤ በሥራህ ሁሉና በጎዳናህ ሁሉ ያከናውንልሃል። በጎውን ሁሉ ከሚሰጥ ከእርሱ ከእግዚአብሔር በቀር ከእግዚአብሔር ያልሆነ አሕዛብ ሁሉ የሚመክሩት ምክር ከንቱ ነውና። የወደደውን ያዋርደዋል፤ እርሱም እንደ ወደደ ይሆናል። አሁንም ልጄ ሆይ ትእዛዜን አስብ፤ ከልብህም አይጥፋ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ሁልጊዜ ጌታ እግዚአብሔርን አመስግን፤ መንገድህን ሁሉ እንዲያቃናልህ ጎዳናህንና ትልምህን ወደ ፍጻሜ እንዲያደርሰው ለምነው። ጥበብ የሁሉም ሕዝብ ሀብት አይደለምና፤ ነገር ግን መልካም ነገሮችን ጌታ ይሰጣል፤ እንደ ፈቃዱ ከፍ ያደርጋል ወይም ሙታን ወደሚኖሩበት ጥልቅ ይጥላል፥ አሁንም ልጄ ሆይ እነዚህን ምክሮች አስታውሳቸው፥ ከልብህም አይጥፉ። ምዕራፉን ተመልከት |