ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ሩፋኤልንም ላከው፤ ሁለቱን ያድናቸው ዘንድ፥ ከጦቢትም ዐይን ብልዙን ያጠፋለት ዘንድ፥ የራጉኤል ልጅ ሳራንም ሚስት ልትሆነው ለጦቢት ልጅ ለጦብያ ይሰጣት ዘንድ፥ ክፉ ጋኔን አስማንድዮስንም ይሽረው ዘንድ፥ ጦብያ ይወርሳታልና። በዚያም ወራት ጦቢት ተመልሶ ወደ ቤቱ ገባ፤ የራጉኤል ልጅ ሳራም ከሰገነቷ ወረደች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ሁለቱንም እንዲፈውሳቸው ሩፋኤል ተላከ። ከጦቢት ዐይን የእግዚአብሔርን ብርሃን እንዲያይ ዓይኑ ላይ ያለውን ነጥብ ሊያጠፋለት፥ የራጉኤል ልጅ ሣራን ደግሞ ለጦቢት ልጅ ለጦብያ በሙሽርነት በመስጠት፥ ከአጋንንት ሁሉ ከከፋው ከአስሞዴዩስ ለማስጣል፥ በእርግጥም ከሁሉም አድናቂዎች ይልቅ የምትገባው ለጦብያ ነበርና፤ በተመሳሳይ ጊዜ ጦቢት ከግቢው አጥር ሲመለስ ሳለ የራጉኤል ልጅ ሣራ ከነበረችበት ክፍል ወደ ታች ደረጃውን በመውረድ ላይ ነበረች። ምዕራፉን ተመልከት |