ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 በተማረክሁበትም ሀገር ስሜንና ያባቴን ስም አላሳደፍሁም፤ እኔም ለአባቴ አንዲት ነኝ። ወንድም የለኝም፤ ሚስት እሆንለት ዘንድ የምጠብቀው የቅርብ ዘመድም የለኝም፤ ሰባቱ ባሎች ሙተውብኛልና እንግዲህ ለምን እኖራለሁ? ልትገድለኝ ባትወድ ግን ወደ እኔ ተመልክተህ ራራልኝ፤ ተግዳሮትንም እንዳልሰማ እዘዝልኝ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በስደት ምድር ላይ የራሴንም ስም ሆነ የአባቴን ስም አላጎገፍኩም፤ ለአባቴም ብቸኛ ልጁ ነኝ፥ የሚወርሰው ሌላ ልጅ የለውም፥ እንዲሁም በአጠገቡ ወንድም የለውም፤ እራሴን የማቆይለት ዘመድም የለውም፤ እስከ አሁን ሰባት ባሎች ሞተውብኛል፥ ታዲያ ከዚህ በኋላ ለምን እኖራለሁ? ነፍሴን ለመው ካላስደሰትህ ግን ጌታ ሆይ እዘንልኝ፥ ከዚህ በኋላ ስሜ ሲጠፋ መስማት አልሻም።” ምዕራፉን ተመልከት |