ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ሩፋኤልም ያንጊዜ ሁለቱን ሁሉ ጠራቸው፤ ገለል አድርጎም እንዲህ አላቸው፥ “እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ ለእርሱም ተገዙ፤ ለስሙም ምስጋና አቅርቡ፤ ስላደረገላችሁም በጎ ነገር ሁሉ በሰው ሁሉ ፊት እመኑበት፤ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ ስሙንም አመስግኑ፤ የእግዚአብሔርንም ሥራ በክብር ተናገሩ፤ ተአምራቱንም ግለጡ፤ እርሱንም ከማመስገን ቸል አትበሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 በዚያን ጊዜ ሩፋኤል ሁለቱንም ለብቻቸው ገለል አደረገና እንዲህ አላቸው፦ “እግዚአብሔርን ባርኩ፥ ያደረገላችሁንም በሕያዋን ሁሉ ፊት ምስጋናውን አውሩ፥ ስሙንም ባርኩ፥ አመስግኑም። የእግዚአብሔርን ሥራ ለሰዎች ሁሉ በሚገባ አስታወቁ፥ እሱን ከማመስገን ቸል አትበሉ። ምዕራፉን ተመልከት |