ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 47:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ሰሎሞንም እንደ አባቶቹ አረፈ ከእርሱም በኋላ አእምሮ የሌለው ልጁን ለእስራኤል ተወ። ይኸውም ሕዝቡን በምክሩ ያሳመፃቸው ሮብዓም ነው። እስራኤልን ያሳታቸው፥ ለኤፍሬምም የኀጢአት መንገድን ያሳየ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ሰሎሞን ከአባቶቹ ጐን አረፈ፥ ዙፋኑን ለልጆቹ አንዱ፥ ከሕዝቡ መካከል እጅግ የማይረባው፥ ማስተዋል የጐደለውና ሕዝቡንም ለዓመፅ የገፋፋው ሮብዓም ወረሰ። ምዕራፉን ተመልከት |