ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 37:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ከሴት ጋር ስለሚያስቀናት ነገር አትናገር፤ ስለ ጦርነትም ከፈሪ ሰው ጋር አትማከር። ስለ ትርፍም ከሻጭ ጋር አትማከር፤ ስለ ንግድ ነገርም ከነጋዴ ጋር አትማከር። ስለ ምጽዋትም ከንፉግ ሰው ጋር አትማከር። ዋጋን ስለ መመለስም ከከዳተኛ ጋር አትማከር፤ ስለ ሥራም ከሰነፍ ሰው ጋራ አትማከር፤ ሥራ ስለሚፈጸምበት ዓመትም ከምንደኛ ጋር አትማከር። ስለ ጥበብም ከአላዋቂ ሰው ጋር አትማከር፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ስለዚህ ነገር የምትማከረው አይኑር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ሴትን ስለጣውንቷ፥ ፊሪን ስለ ጦርነት፥ ነጋዴን ስለዋጋ፥ ሸማችን ስለገበያ፥ ባለጌን ስለ ውለታ፥ ራስ ወዳዱን ስለ ደግነት፥ ሰነፉን ስለ ሥራ፥ ዳተኛውን ስለ ሥራው ፍጻሜ፥ ሀኬተኛውን አገልገይ ስለ አስቸጋሪው ሥራ አትጠይቃቸው። ከእነርሱ የሚመጣውንም ምክር አትቀበል። ምዕራፉን ተመልከት |