ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 22:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ነገር ግን ብትላገድበት፥ አፍህንም በእርሱ ላይ ከፍና ዝቅ አድርገህ ብትናገር፥ ብትሰድበውም፥ ምክሩንም ብታወጣበት፥ ብትከዳውና፥ ብታሳዝነው በዚህ ነገር ወዳጅ ሁሉ ይሸሻል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ባልንጀራህ ላይ ክፉ ብትናገር እርቅ ይወርደ ዘንድ ተስፋ ስላለ አትጨነቅ፤ ብትሰድበው፥ ሐሳበ-ግትር ብትሆንበት፥ ምሥጢሩን ብትገልጽበትና ከጀርባው ብትወጋው ግን ባልንጀራህን እንደምታጣ እወቅ። ምዕራፉን ተመልከት |