Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሩት 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እንግዲህ ታጠቢ፥ ተቀቢ፥ ልብስሽን ተላበሺ፥ ወደ አውድማውም ውረጂ፣ ነገር ግን መብሉንና መጠጡን እስኪጨርስ ድረስ ለሰውዮው አትታዪው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ተጣጠቢ፤ ሽቱ ተቀቢ፤ እንዲሁም የክት ልብስሽን ልበሺ፤ ከዚያም ወደ ዐውድማው ውረጂ፤ ይሁን እንጂ በልቶና ጠጥቶ እስኪያበቃ ድረስ፣ እዚያ መሆንሽን እንዳያውቅ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እንግዲህ ሰውነትሽን ታጠቢና ሽቶ ተቀቢ፥ የክት ልብስሽንም ልበሺ፥ ከዚህ በኋላ እርሱ ገብሱን ወደሚወቃበት አውድማ ሂጂ፤ ነገር ግን እስከሚበላና እስከሚጠጣ ድረስ በፊቱ አትታዪ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለዚህ ሰውነትሽን ታጠቢና ሽቶ ተቀቢ፤ የክት ልብስሽንም ልበሺ፤ ከዚህ በኋላ እርሱ ገብሱን ወደሚወቃበት አውድማ ሂጂ፤ ነገር ግን እስከሚበላና እስከሚጠጣ ድረስ በፊቱ አትታዪ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እንግዲህ ታጠቢ፤ ተቀቢ፤ ልብስሽን ተላበሺ፤ ወደ አውድማውም ውረጂ፤ ነገር ግን መብሉንና መጠጡን እስኪጨርስ ድረስ ለሰውዮው አትታዪው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሩት 3:3
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም ከም​ድር ተነ​ሥቶ ታጠበ፤ ተቀ​ባም፤ ልብ​ሱ​ንም ለወጠ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ገብቶ ሰገደ። ወደ ቤቱም መጣ፦ እን​ጀ​ራም አም​ጡ​ልኝ አለ፤ በፊ​ቱም እን​ጀራ አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ በላም።


ኢዮ​አ​ብም ወደ ቴቁሔ ልኮ ከዚያ ብል​ሃ​ተኛ ሴት አስ​መ​ጣና፥ “አል​ቅሺ፤ የኀ​ዘ​ንም ልብስ ልበሺ፤ ዘይ​ትም አት​ቀቢ፤ ስለ ሞተ ሰውም ብዙ ዘመን እን​ደ​ም​ታ​ለ​ቅስ ሴት ሁኚ፤


የቀ​ባ​ኋ​ቸ​ውን አት​ዳ​ስሱ፥ በነ​ቢ​ያ​ቴም ላይ ክፉ አታ​ድ​ርጉ።


ሁል​ጊዜ ልብ​ስህ ነጭ ይሁን፤ ቅባ​ትም ከራ​ስህ ላይ አይ​ታጣ።


በው​ኃም አጠ​ብ​ሁሽ፤ ከደ​ም​ሽም አጠ​ራ​ሁሽ፤ በዘ​ይ​ትም ቀባ​ሁሽ።


አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ፤ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።


አሁንም ከገረዶቹ ጋር የነበርሽበት ቦዔዝ ዘመዳችን አይደለምን? እነሆ፥ እርሱ በዛሬ ሌሊት በአውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል።


በተኛም ጊዜ የሚተኛበትን ስፍራ ተመልከቺ፥ ገብተሽም እግሩን ግለጪ፥ ተጋደሚም፣ የምታደርጊውንም እርሱ ይነግርሻል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች