Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሩት 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ወደሚያጭዱበትም ስፍራ ተመልከቺ፥ ተከተያቸውም፣ እንዳያስቸግሩሽም ጐበዛዝቱን አዝዣለሁ፣ በተጠማሽም ጊዜ ወደ ማድጋው ሄደሽ ጐበዛዝቱ ከቀዱት ውኃ ጠጪ አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ወንዶቹ የሚያጭዱበትን ዕርሻ ልብ እያልሽ ልጃገረዶቹን ተከተዪ፤ ወንዶቹ እንዳያስቸግሩሽም አስጠንቅቄአቸዋለሁ፤ ውሃ ሲጠማሽ ደግሞ፣ እየሄድሽ ወንዶቹ ሞልተው ካስቀመጡት እንስራ ቀድተሽ ጠጪ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ወደሚያጭዱበትም ስፍራ ተመልከቺ፥ ተከተያቸውም፥ እንዳያስቸግሩሽም ጐበዛዝቱን አዝዣለሁ፥ በተጠማሽም ጊዜ ወደ ማድጋው ሄደሽ ጐበዛዝቱ ከቀዱት ውኃ ጠጪ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እነርሱ የት እንደሚያጭዱ በመጠባበቅ እየተመለከትሽ ከእነርሱ ጋር ሁኚ፤ ወንዶች ሠራተኞቼን እንዳያስቸግሩሽ አስጠንቅቄአቸዋለሁ፤ ውሃም በሚጠማሽ ጊዜ እነርሱ ሞልተው ወዳስቀመጡአቸው እንስራዎች እየሄድሽ ቀድተሽ ጠጪ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ወደሚያጭዱበትም ስፍራ ተመልከቺ፤ ተከተያቸውም፤ እንዳያስቸግሩሽም ጐበዛዝቱን አዝዣለሁ፤ በተጠማሽም ጊዜ ወደ ማድጋው ሄደሽ ጐበዛዝቱ ከቀዱት ውሃ ጠጪ፤” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሩት 2:9
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም አለው፥ “ይህን በል​ብህ ቅን​ነት እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እኔ ዐወ​ቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢ​አ​ትን እን​ዳ​ት​ሠራ ጠበ​ቅ​ሁህ፤ ስለ​ዚ​ህም ትቀ​ር​ባት ዘንድ አል​ተ​ው​ሁ​ህም።


ስለ ጻፋ​ች​ሁ​ል​ኝስ ለሰው ወደ ሴት አለ​መ​ቅ​ረብ ይሻ​ለ​ዋል።


ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።”


ወደ ጐልማሳ ሚስት የሚገባም እንዲሁ ነው፤ የሚነካትም ሁሉ አይነጻም።


የለ​መ​ኑ​ት​ንም ሰጣ​ቸው፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ውም ጥጋ​ብን ላከ።


እና​ንተ ወዳ​ጆቼ ሆይ፤ ማሩኝ፤ ማሩኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ዳስ​ሳ​ኛ​ለ​ችና።


ቦዔዝም ሩትን፦ ልጄ ሆይ፥ ትሰሚያለሽን? ቃርሚያ ለመቃረም ወደ ሌላ እርሻ አትሂጂ፥ ከዚህም አትላወሺ፥ ነገር ግን ገረዶቼን ተጠጊ።


በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፦ እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን? አለችው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች