Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ራእይ 17:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ፤” ብሎ ተናገረኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የምድር ነገሥታት ከርሷ ጋራ አመነዘሩ፤ የምድር ነዋሪዎችም በዝሙቷ የወይን ጠጅ ሰከሩ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የምድርም ነገሥታት ከእርሷ ጋር ሴሰኑ፤ በምድርም የሚኖሩ በዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ፤” ብሎ ተናገረኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የምድር ነገሥታት ከእርስዋ ጋር አመንዝረዋል፤ የምድር ኗሪዎችም በአመንዝራነትዋ የወይን ጠጅ ሰክረዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ ብሎ ተናገረኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ራእይ 17:2
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባቢ​ሎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ውስጥ ምድ​ርን ሁሉ ያሰ​ከ​ረች የወ​ርቅ ጽዋ ነበ​ረች፤ አሕ​ዛ​ብም ከጠ​ጅዋ ጠጥ​ተ​ዋል፤ ስለ​ዚህ አሕ​ዛብ ተን​ገ​ዳ​ግ​ደ​ዋል።


ስለ ተዋበችው ጋለሞታ ግልሙትና ብዛት ይህ ሆኖአል፣ እርስዋም በመተትዋ እጅግ በለጠች፥ አሕዛብንም በግልሙትናዋ፥ ወገኖችንም በመተትዋ ሸጠች።


አሳ​ዳ​ሪ​ውም ሙሽ​ራ​ውን ጠርቶ፥ “ሰው ሁሉ መል​ካ​ሙን የወ​ይን ጠጅ አስ​ቀ​ድሞ ያጠ​ጣል፤ ከጠ​ገቡ በኋ​ላም ተር​ታ​ውን ያመ​ጣል፤ አንተ ግን መል​ካ​ሙን የወ​ይን ጠጅ እስ​ካ​ሁን አቈ​የህ” አለው።


ሌላም ሁለተኛ መልአክ “አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው።


እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፤ ኀይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።


እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አገብቶአልና።


በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም “ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት” ተብሎ ተጻፈ።


ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፤ አሁንም የለም፤ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።


የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”


አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሣ ወድቀዋልና፤ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ፤ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኀይል የተነሣ ባለጠጋዎች ሆኑ፤” ብሎ ጮኸ።


ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ እየጮሁ እያሉ ያለቅሳሉ፤


እነሆ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፤ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሓ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ፤


የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።


ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሓ አልገቡም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች