Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 68:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ለወ​ን​ድ​ሞቼ እንደ ባዕድ፥ ለአ​ባ​ቴና ለእ​ና​ቴም ልጆች እንደ እን​ግዳ ሆን​ሁ​ባ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በሲና አምላክ፣ በእግዚአብሔር ፊት፣ በእስራኤል አምላክ፣ በእግዚአብሔር ፊት፣ ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዶፍ አወረዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አቤቱ፥ በሕዝብህ ፊት በወጣህ ጊዜ፥ በምድረ በዳም ባለፍህ ጊዜ፥ ምድር ተናወጠች፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የሲና አምላክ በመምጣቱ፥ የእስራኤል አምላክ በመገለጡ፥ ምድር ተናወጠች፤ ሰማይም ዝናብን አዘነበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 68:8
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት ስለ ወረ​ደ​በት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም ሁሉ እጅግ ይና​ወጥ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጽ​መው ደነ​ገጡ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን በማ​ለዳ ጊዜ ነጐ​ድ​ጓ​ድና መብ​ረቅ፥ ከባ​ድም ደመና፥ ጉምም በሲና ተራራ ላይ ሆነ፤ እጅ​ግም የበ​ረታ የቀ​ንደ መለ​ከት ድምፅ ተሰማ፤ በሰ​ፈ​ሩም የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ።


ያን​ጊዜ ቃል ምድ​ርን አና​ወ​ጣት፤ “አሁ​ንም እኔ ምድ​ርን እንደ ገና አንድ ጊዜ አና​ው​ጣ​ታ​ለሁ” ብሎ ተና​ገረ፤ ምድ​ርን ብቻም አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ይ​ንም ጭምር እንጂ።


በስ​ም​ህም የም​ጠ​ራህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨ​ለማ የነ​በ​ሩ​ትን መዛ​ግ​ብት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ የማ​ይ​ታ​የ​ው​ንም የተ​ደ​በ​ቀ​ውን ሀብት እገ​ል​ጥ​ል​ሃ​ለሁ።


ለነ​ፍ​ሳ​ቸው መብ​ልን ይፈ​ልጉ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በል​ባ​ቸው ፈተ​ኑት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን አድ​ኗ​ታ​ልና፥ የይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ይሠ​ራ​ሉና፤ በዚ​ያም ይቀ​መ​ጣሉ ይወ​ር​ሷ​ታ​ልም።


የክ​ብ​ር​ህ​ንም ሥራ ባደ​ረ​ግህ ጊዜ፥ ተራ​ሮች በፊ​ትህ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ።


ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረ​ፍ​ትሽ ተመ​ለሺ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ትሽ ነውና፤


በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።


ሕዝብህን ለመታደግ፥ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፣ የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፣ መሠረቱን እስከ አንገቱ ድረስ ገለጥህ።


ሰማ​ይን ብት​ከ​ፍት ከአ​ንተ የተ​ነሣ ተራ​ሮች ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ይቀ​ል​ጣ​ሉም።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን በዙ​ሪያ መን​ገድ በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለ​ችው ምድረ በዳ መራ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ትው​ልድ ከግ​ብፅ ምድር ወጡ።


ዲቦ​ራም ባር​ቅን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲሣ​ራን በእ​ጅህ አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጥ​በት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፤ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ ይሄ​ዳል” አለ​ችው። ባር​ቅም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከ​ት​ለ​ውት ከታ​ቦር ተራራ ወረደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች