Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 65:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ በሉት፥ “ሥራህ ግሩም ነው፤ ኀይ​ልህ ብዙ ሲሆን ጠላ​ቶ​ችህ ዋሹ​ብህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ኀጢአት ባጥለቀለቀን ጊዜ፣ አንተ መተላለፋችንን ይቅር አልህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ሥጋ ሁሉ ይመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኃጢአት በላያችን በርትቶብን ነበር፤ አንተ ግን በደላችንን ሁሉ ይቅር አልክልን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 65:3
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “በፊቴ የጸ​ለ​ይ​ኸ​ውን ጸሎ​ት​ህ​ንና ልመ​ና​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እንደ ጸሎ​ት​ህም ሁሉ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠ​ራ​ኸ​ውን ቤት ቀድ​ሻ​ለሁ፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም በዘ​መኑ ሁሉ በዚያ ይሆ​ናሉ።


የአ​ሞ​ጽም ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ እን​ዲህ ብሎ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ላከ፥ “የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰና​ክ​ሬም ወደ እኔ የለ​መ​ን​ኸ​ውን ሰም​ቻ​ለሁ።


“ተመ​ል​ሰህ የሕ​ዝ​ቤን ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በለው፦ የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፥ እን​ባ​ህ​ንም አይ​ቻ​ለሁ፤ እነሆ፥ እኔ እፈ​ው​ስ​ሃ​ለሁ፤ እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ትወ​ጣ​ለህ።


“አቤቱ፥ ፍጻ​ሜ​ዬን አስ​ታ​ው​ቀኝ” አልሁ፥ የዘ​መኔ ቍጥ​ሮች ምን ያህል ናቸው? ዐውቅ ዘን​ድስ ለምን ወደ ኋላ እላ​ለሁ?


እኔን ግን ስለ የዋ​ህ​ነቴ ተቀ​በ​ል​ኸኝ፥ በፊ​ት​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ኸኝ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረዳቱ ያላ​ደ​ረገ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ቱም ብዛት የታ​መነ፥ በከ​ንቱ ነገ​ርም የበ​ረታ ያ ሰው እነሆ።”


በፊ​ቷም መን​ገ​ድን ጠረ​ግህ፥ ሥሮ​ች​ዋ​ንም ተከ​ልህ፥ ምድ​ር​ንም ሞላች።


አፌ​ንም ዳሰ​ሰ​በ​ትና፥ “እነሆ፥ ይህ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህን ነክ​ቶ​አል፤ በደ​ል​ህም ከአ​ንተ ተወ​ገደ፤ ኀጢ​አ​ት​ህም ተሰ​ረ​የ​ልህ” አለኝ።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፦ በየ​መ​ባ​ቻ​ውና በየ​ሰ​ን​በቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በፊቴ ይሰ​ግድ ዘንድ ዘወ​ትር ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ጌታ ሆይ! አንተ ኀይ​ሌና ረዳቴ፥ በመ​ከ​ራም ቀን መጠ​ጊ​ያዬ ነህ፤ ከም​ድር ዳርቻ አሕ​ዛብ ወደ አንተ መጥ​ተው፥ “በእ​ው​ነት አባ​ቶ​ቻ​ችን ውሸ​ት​ንና ከን​ቱን ነገር ለም​ንም የማ​ይ​ረ​ባ​ቸ​ውን ጣዖ​ትን ሠር​ተ​ዋል” ይላሉ።


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ።


ሥጋ መን​ፈስ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ መን​ፈ​ስም ሥጋ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ የም​ት​ሹ​ት​ንም እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እርስ በር​ሳ​ቸው ይጣ​ላሉ።


ነውር የሌ​ለው ሆኖ፥ በዘ​ለ​ዓ​ለም መን​ፈስ ራሱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረበ የክ​ር​ስ​ቶስ ደም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ከው ዘንድ ሕሊ​ና​ች​ንን ከሞት ሥራ እን​ዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች