መዝሙር 58:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 አምላክ ሆይ፤ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንበሶቹን መንጋጋ አወላልቅ! ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 አስማተኛ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 አምላክ ሆይ! የእነዚህን እንደ አንበሳ አስፈሪ የሆኑ ሰዎች ጥርስ ስበር፤ መንጋጋቸውንም አውልቅ። ምዕራፉን ተመልከት |
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛልና፥ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ እንደሚያገሣ፥ ድምፁም ተራሮችን እስኪሞላ በእርሱ ላይ እንደሚጮህ፥ እረኞችም ሁሉ ሲጮሁበት ከብዛታቸው የተነሣ እንደማይፈራ፥ ከድምፃቸውም የተነሣ እንደማይደነግጥ፥ እነርሱም ከቍጣው ብዛት የተነሣ ድል እንደሚሆኑና እንደሚደነግጡ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።