Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 51:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እኔስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ለመ​ለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤ ለዓ​ለ​ምና ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረት ታመ​ንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፤ ያደቀቅሃቸው ዐጥንቶቼም ደስ ይበላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፥ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የሰበርካቸውን አጥንቶቼን አድሰህ የደስታንና የሐሤትን ድምፅ አሰማኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 51:8
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አም​ላኬ ሆይ፥ ልብን እን​ደ​ም​ት​መ​ረ​ምር፥ ጽድ​ቅ​ንም እን​ደ​ም​ት​ወ​ድድ አው​ቃ​ለሁ፤ እኔም በልቤ ቅን​ነ​ትና በፈ​ቃዴ ይህን ሁሉ አቅ​ር​ቤ​አ​ለሁ፤ አሁ​ንም በዚህ ያለው ሕዝ​ብህ በፈ​ቃዱ እን​ዳ​ቀ​ረ​በ​ልህ በደ​ስታ አይ​ቻ​ለሁ።


ከከ​ን​ፈ​ራ​ቸው በታች የእ​ባብ መርዝ አለ፤ አፋ​ቸው መራራ ነው፥ መር​ገ​ም​ንም ተሞ​ል​ቶ​አል፤


በጠ​ላ​ቶቼ ሁሉ ዘንድ ተሰ​ደ​ብሁ፥ ይል​ቁ​ንም በጎ​ረ​ቤ​ቶቼ ዘንድ፥ ለዘ​መ​ዶ​ቼም አስ​ፈሪ ሆንሁ፤ በሜዳ ያዩ​ኝም ከእኔ ሸሹ።


ምሕ​ረ​ት​ህን በሚ​ያ​ው​ቁህ ላይ፥ ጽድ​ቅ​ህ​ንም በልበ ቅኖች ላይ ዘርጋ።


ልቤም በው​ስጤ ሞቀ​ብኝ፤ ከመ​ና​ገ​ሬም የተ​ነሣ እሳት ነደደ፥ በአ​ን​ደ​በ​ቴም ተና​ገ​ርሁ፦


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ይመ​ለ​ሳሉ፤ በደ​ስ​ታም ተመ​ል​ሰው ወደ ጽዮን ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታም በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታ​ንም ያገ​ኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘ​ንና ትካ​ዜም ይጠ​ፋሉ።


አቤቱ! ዐይ​ኖ​ችህ ለሃ​ይ​ማ​ኖት አይ​ደ​ሉ​ምን? አንተ ቀሥ​ፈ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ነገር ግን አላ​ዘ​ኑም፤ ቀጥ​ቅ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ማል፤ ነገር ግን ተግ​ሣ​ጽን እንቢ አሉ፤ ፊታ​ቸ​ውን ከድ​ን​ጋይ ይልቅ አጠ​ን​ክ​ረ​ዋል፤ ይመ​ለ​ሱም ዘንድ እንቢ አሉ።


የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤መፅናናትን ያገኛሉና።


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በላዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ቀብቶ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን እሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ያዘ​ኑ​ት​ንም ደስ አሰ​ኛ​ቸው ዘንድ፥ ዕው​ሮ​ችም ያዩ ዘንድ፥ የተ​ገ​ፉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የታ​ሰ​ሩ​ት​ንም እፈ​ታ​ቸው ዘንድ፥ የቈ​ሰ​ሉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች