Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 45:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ፈሳሽ ወንዝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከተማ ደስ ያሰ​ኛል፤ ልዑል ማደ​ሪ​ያ​ውን ቀደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለ እውነት፣ ስለ ትሕትና፣ ስለ ጽድቅ ሞገስን ተጐናጽፈህ በድል አድራጊነት ገሥግሥ፤ ቀኝ እጅህም ድንቅ ተግባር ታሳይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ኃያል ሆይ፥ በግርማህና በውበትህ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ስለ እውነትና ስለ ፍትሕ ግርማን ተጐናጽፈህ ድል ለማድረግ ገሥግሥ፤ ኀይልህም ታላላቅ ድሎችን ያስገኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 45:4
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በብ​ረት በትር ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”


በድ​ን​ኳ​ንህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኖ​ራ​ለሁ፤ በክ​ን​ፎ​ችህ ጥላም እጋ​ረ​ዳ​ለሁ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ታዩ ዘንድ ኑ። ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ግሩም ነው።


ወገ​ቡን በጽ​ድቅ ይታ​ጠ​ቃል፤ እው​ነ​ት​ንም በጎኑ ይጐ​ና​ጸ​ፋል።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤


ነገር ግን እነ​ዚ​ያን ልነ​ግ​ሥ​ባ​ቸው ያል​ወ​ደ​ዱ​ትን ጠላ​ቶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጡና በፊቴ ውጉ​አ​ቸው።”


ኦሪት በሙሴ ተሰ​ጥ​ታን ነበ​ርና፤ ጸጋና እው​ነት ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆነ​ልን።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ው​ነ​ትና የሕ​ይ​ወት መን​ገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካል​ሆነ በቀር ወደ አብ የሚ​መጣ የለም።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ጳው​ሎስ በእ​ና​ንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆ​ንሁ፥ ከእ​ና​ንተ ብርቅ ግን የም​ደ​ፍ​ራ​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ቸር​ነት እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፥ በፍ​ቅ​ራ​ችሁ እታ​መ​ና​ለ​ሁና።


ወንጌላችን በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።


ስለዚህም የመልእክትን ቃል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በምታምኑ ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።


በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! የጌታ ቃል እንዲሮጥ፥ በእናንተም ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር፥ እምነትም ለሁሉ ስለማይሆን ከዐመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ እኛ ጸልዩ።


አሕዛብም ተቈጡ፤ ቍጣህም መጣ፤ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፤ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።”


ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።


አየሁም፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፤ አክሊልም ተሰጠው፤ ድልም እየነሣ ወጣ፤ ድል ለመንሣት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች