Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እና​ገር ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለኝ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የእግዚአብሔርን ሕግ ዐውጃለሁ፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ትእዛዙን እናገራለሁ፥ ጌታ አለኝ፦ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “የእግዚአብሔርን ዐዋጅ ዐውጃለሁ፤ እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 2:7
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲሁ ክር​ስ​ቶ​ስም ሊቀ ካህ​ናት ይሆን ዘንድ ራሱን ያከ​በረ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ” ያለው እርሱ ራሱ ነው።


በሁ​ለ​ተ​ኛው መዝ​ሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ’ እን​ዳለ ኢየ​ሱ​ስን አስ​ነ​ሥቶ ተስ​ፋ​ውን ለእኛ ለል​ጆ​ቻ​ቸው ፈጽ​ሞ​አል።


እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።


እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ በኀ​ይ​ሉና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ ከሙ​ታ​ንም ተለ​ይቶ በመ​ነ​ሣቱ ስለ አሳየ ስለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ፥


በእ​ርሱ የሚ​ያ​ምን ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኝ እንጂ እን​ዳ​ይ​ጠፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ድያ ልጁን ቤዛ አድ​ርጎ እስ​ኪ​ሰጥ ድረስ ዓለ​ሙን እን​ዲህ ወዶ​ታ​ልና።


ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእ​ኛም አደረ፤ ለአ​ባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብ​ሩን አየን፤ ጸጋ​ንና እው​ነ​ትን የተ​መላ ነው።


ክር​ስ​ቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታ​መነ ነው፤ እኛም የም​ን​ደ​ፍ​ር​በ​ትን፥ የም​ን​መ​ካ​በ​ት​ንም ተስፋ እስከ መጨ​ረ​ሻው አጽ​ን​ተን ብን​ጠ​ብቅ ቤቱ ነን።


በአ​ባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጅ እርሱ ገለ​ጠ​ልን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ከቶ ያየው የለም።


ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” አለ።


ልጅም ቢሆን መከ​ራን ስለ ተቀ​በለ መታ​ዘ​ዝን ዐወቀ።


እነሆም “ኢየሱስ ሆይ! የእግዚአብሔር ልጅ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?” እያሉ ጮኹ።


በመ​ጀ​መ​ሪያ መጨ​ረ​ሻ​ውን፥ ከጥ​ን​ትም ያል​ተ​ደ​ረ​ገ​ውን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ምክሬ ትጸ​ና​ለች፤ የመ​ከ​ር​ሁ​ት​ንም ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ እላ​ለሁ።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም አቆ​ማ​ቸው፤ ትእ​ዛ​ዝን ሰጣ​ቸው፥ አላ​ለ​ፉ​ምም።


“ስለ ፍርድ የሚ​ከ​ራ​ከር ማን ነው? እርሱ የወ​ደ​ደ​ውን ያደ​ር​ጋ​ልና።


በመ​ን​ገድ ሲሄ​ዱም ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “እነሆ፥ ውኃ፥ መጠ​መ​ቅን ምን ይከ​ለ​ክ​ለ​ኛል?” አለው።


እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ልጅ ይሆ​ነ​ኛል፤ ክፉ ነገ​ርም ቢያ​ደ​ርግ፥ በሰ​ዎች በት​ርና በሰው ልጆች አለ​ንጋ እገ​ሥ​ጸ​ዋ​ለሁ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች