Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 18:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ንጹሕ ነው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይኖ​ራል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ እው​ነ​ትና ቅን​ነት በአ​ን​ድ​ነት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፥ ከአፉም የሚበላ እሳት ነደደ፥ ፍምም ከእርሱ በራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሰማይን ሰንጥቆ ወደ ታች ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 18:9
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰማ​ዮ​ችን አዘ​ነ​በለ፤ ወረ​ደም፤ ጭጋ​ግም ከእ​ግሩ በታች ነበረ።


እኔ በደ​ሌን አው​ቃ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ቴም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነውና።


በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፤ በዐ​መፅ የሚ​ከ​ብ​ቡኝ ጠላ​ቶቼ በረቱ፤ ያል​ወ​ሰ​ድ​ሁ​ትን ይከ​ፈ​ሉ​ኛል።


ለያ​ዕ​ቆብ ይቅ​ር​ታ​ውን ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት እው​ነ​ቱን አሰበ፤ የም​ድር ዳር​ቻ​ዎች ሁሉ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ማዳን እዩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት ስለ ወረ​ደ​በት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም ሁሉ እጅግ ይና​ወጥ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጽ​መው ደነ​ገጡ።


ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁን ወደ ሰማይ አንሡ፤ ወደ ታችም ወደ ምድር ተመ​ል​ከቱ፤ ሰማ​ያት እንደ ጢስ በን​ነው ይጠ​ፋሉ፤ ምድ​ርም እንደ ልብስ ታረ​ጃ​ለች፤ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም እን​ዲሁ ይሞ​ታሉ፤ ማዳ​ኔም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ናት፤ ጽድ​ቄም አታ​ል​ቅም።


እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቱን በቍጣ፥ ዘለ​ፋ​ው​ንም በእ​ሳት ነበ​ል​ባል ይመ​ልስ ዘንድ እንደ እሳት ይመ​ጣል፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆ​ናሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይጮ​ኻል፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ ሰማ​ይና ምድ​ርም ይና​ወ​ጣሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ለሕ​ዝቡ ይራ​ራል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ያጸ​ናል።


“ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤


ስድስት ሰዓትም በሆነ ጊዜ፥ እስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የም​ሠ​ራ​ውን አንተ ዛሬ አታ​ው​ቅም፤ ኋላ ግን ታስ​ተ​ው​ለ​ዋ​ለህ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


እንደ ፍቁሩ አም​ላክ ማንም የለም፤ በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው፥ በጠ​ፈ​ርም በታ​ላ​ቅ​ነት ያለው እርሱ ረዳ​ትህ ነው።


ያን​ጊዜ ቃል ምድ​ርን አና​ወ​ጣት፤ “አሁ​ንም እኔ ምድ​ርን እንደ ገና አንድ ጊዜ አና​ው​ጣ​ታ​ለሁ” ብሎ ተና​ገረ፤ ምድ​ርን ብቻም አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ይ​ንም ጭምር እንጂ።


የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፤ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።


ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች