Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከቍ​ጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊ​ቱም እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእ​ርሱ በራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህም ጥላ ሰውረኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፥ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የዐይን ብሌን በጥንቃቄ የሚጠበቀውን ያኽል ጠብቀኝ፤ በጥበቃህ ውስጥ ሰውረኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 17:8
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ ጽድ​ቄን ስማኝ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም አድ​ም​ጠኝ፤ በተ​ን​ኰ​ለ​ኛም ከን​ፈር ያል​ሆ​ነ​ውን ጸሎ​ቴን አድ​ም​ጠኝ፤


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዛ አገ​ል​ግ​ለ​ውም። በሕ​ይ​ወቱ ደስ ባለ​ውና ዐመ​ፃን በሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው ላይ አት​ቅና።


መዓ​ትን ተዋት፤ ቍጣ​ንም ጣላት፥ እን​ዳ​ት​በ​ድ​ልም አት​ቅና።


በእ​ው​ነት ጽድ​ቅን ብት​ና​ገ​ሩስ፥ የሰው ልጆች ሆይ፥ በቅን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ፤


በል​ባ​ችሁ በም​ድር ላይ ኀጢ​አ​ትን ትሠ​ራ​ላ​ች​ሁና፥ እጆ​ቻ​ች​ሁም ሽን​ገ​ላን ይታ​ታ​ሉና።


ነገር ግን ክብ​ሬን ይሽሩ ዘንድ መከሩ፥ በጥ​ሜም ሮጥሁ፤ በአ​ፋ​ቸው ይባ​ር​ካሉ፥ በል​ባ​ቸ​ውም ይረ​ግ​ማሉ።


ነገር ግን ነፍሴ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትገ​ዛ​ለች፥ ተስ​ፋዬ ከእ​ርሱ ዘንድ ናትና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፍ ከፍ ይላል። መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸው እንደ ልጆች ሕንፃ ሆነ፤


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን ይሻ​ላል፥ ልዑል ሆይ፥ ለስ​ም​ህም መዘ​መር፤


አቤቱ፥ በሥ​ራህ ደስ አሰ​ኝ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፤ በእ​ጆ​ች​ህም ሥራ ደስ ይለ​ኛ​ልና።


ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርን አክብረው ትጸናለህም። ከእርሱ በቀር ሌላውን አትፍራ፥ ከእርሱ በቀር የሚገድልህም የሚያድንህም የለምና። ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፤ ቃሌንም እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቅ፤


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ በዘበዙአችሁ አሕዛብ ልኮኛል፣ የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና።


“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።


“ነቢ​ያ​ትን የም​ት​ገ​ድ​ሊ​ያ​ቸው፥ ወደ አንቺ የተ​ላ​ኩ​ትን ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም የም​ት​ደ​በ​ድ​ቢ​ያ​ቸው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዶሮ ጫጩ​ቶ​ች​ዋን ከክ​ን​ፍዋ በታች እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ ልጆ​ች​ሽን ልሰ​በ​ስ​ባ​ቸው ምን ያህል ወደ​ድሁ? ነገር ግን እንቢ አላ​ችሁ።


በም​ድረ በዳ አጠ​ገ​ባ​ቸው፤ በጥ​ማ​ትና በድ​ካም ቦታ፥ በው​ድማ ከበ​ባ​ቸው፤ መገ​ባ​ቸው፤ መራ​ቸ​ውም፤ እንደ ዐይን ብሌ​ንም ጠበ​ቃ​ቸው።


እግዚአብሔር እንደ ሥራሽ ይስጥሽ፣ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝሽ ፍጹም ይሁን አላት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች