መዝሙር 144:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 በየቀኑ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም ለዘለዓለም ዓለም ምስጋና አቀርባለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እርሱ አፍቃሪ አምላኬና ጽኑ ዐምባዬ ነው፤ ምሽጌና ታዳጊዬ፣ የምከለልበትም ጋሻዬ ነው፤ ሕዝቤን የሚያስገዛልኝም እርሱ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 መሓሪዬና መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና መድኃኒቴ፥ ረዳቴና መታመኛዬም፥ ሕዝቤንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እግዚአብሔር ጠባቂዬና መከታዬ ነው፤ መጠለያዬና አዳኜ ነው፤ በእርሱ ተማምኜ በሰላም እኖራለሁ፤ እርሱ አሕዛብን ከእግሬ በታች አድርጎ ያስገዛልኛል። ምዕራፉን ተመልከት |