Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 11:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 “ምላ​ሳ​ች​ንን እና​በ​ረ​ታ​ለን፤ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ችን የእኛ ናቸው፥ ጌታ​ችን ማን ነው?” የሚ​ሉ​ትን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው። ዐይኖቹ ሰዎችን ይመለከታሉ፤ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታ በተቀደሰው መቅደሱ ነው፥ ጌታ፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፥ ዐይኖቹ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ ነው፤ ዙፋኑም በሰማይ ነው፤ የሰውን ልጆች ይመለከታል። አተኲሮም በማየት ዐይኖቹም ይመረምሩአቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 11:4
28 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድ​ን​ኳ​ንና በማ​ደ​ሪያ ኖርሁ እንጂ በቤት ውስጥ አል​ኖ​ር​ሁም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ በእ​ርሱ ዘንድ ፍጹም የሆ​ነ​ውን ያጸና ዘንድ ዐይ​ኖቹ በም​ድር ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታ​ሉና። አሁ​ንም ባለ​ማ​ወ​ቅህ በድ​ለ​ሃል፤ ስለ​ዚ​ህም ከዛሬ ጀምሮ ጦር​ነት ይሆ​ን​ብ​ሃል።”


በታ​መ​መም ጊዜ መዳ​ንን ተስፋ አያ​ደ​ር​ግም። ነገር ግን እርሱ በሕ​ማሙ ይሞ​ታል።


ጨረ​ቃን በጊ​ዜው ፈጠ​ርህ፤ ፀሐ​ይም መግ​ቢ​ያ​ውን ያው​ቃል።


አንቺ ባሕር የሸ​ሸሽ፥ አን​ተም ዮር​ዳ​ኖስ ወደ ኋላህ የተ​መ​ለ​ስህ፥ ምን ሁና​ችሁ ነው?


በቅ​ን​ነት የሚ​ሄድ፥ ጽድ​ቅ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም እው​ነ​ትን የሚ​ና​ገር።


አወ​ጣጡ ከሰ​ማ​ያት ዳርቻ ነው፥ መግ​ቢ​ያ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ነው፤ ከት​ኩ​ሳ​ቱም የሚ​ሰ​ወር የለም።


በሰ​ማይ የሚ​ኖር እርሱ ይሥ​ቅ​ባ​ቸ​ዋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሣ​ለ​ቅ​ባ​ቸ​ዋል።


አን​ደ​በ​ት​ህን ከክፉ ከል​ክል፥ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህም ሽን​ገ​ላን እን​ዳ​ይ​ና​ገሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ከ​ናል፥ የም​ድ​ርም ዳር​ቻ​ዎች ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።


በጽ​ዮን ለሚ​ኖር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ሥራ​ውን ንገሩ፤


የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉ ቦታ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችንም ይመለከታሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድ​ርም የእ​ግሬ መረ​ገጫ ናት፤ የም​ት​ሠ​ሩ​ልኝ ቤት ምን ዓይ​ነት ነው? የማ​ር​ፍ​በ​ትስ ስፍራ ምን​ድን ነው?


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ሁሉ እንደ መን​ገ​ዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመ​ረ​ም​ራ​ለሁ፤ ኵላ​ሊ​ት​ንም እፈ​ት​ና​ለሁ።”


ሰው በስ​ውር ቦታ ቢሸ​ሸግ፥ እኔ አላ​የ​ው​ምን? ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንስ የሞ​ላሁ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ ስሙ፥ ምድርም ሙላዋም ታድምጥ፥ ጌታ እግዚአብሔርም፥ እርሱም በቅዱስ መቅደሱ የሆነ ጌታ፥ ይመስክርባችሁ።


እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፣ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።


እግዚአብሔር ከተቀደሰ ማደሪያው ነቅቶአልና ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሆይ፥ በፊቱ ዝም በል።


በቤተ መቅደስም የሚምለው በእርሱና በእርሱ በሚኖረው ይምላል፤


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ከቶ አትማሉ፤ በሰማይ አይሆንም የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድ​ርም የእ​ግሬ መረ​ገጫ ናት፤ ምን ዐይ​ነት ቤት ትሠ​ሩ​ል​ኛ​ላ​ችሁ? የማ​ር​ፍ​በት ቦታስ ምን ዐይ​ነት ቦታ ነው?


“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤” ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።


እኛን በሚ​ቈ​ጣ​ጠር በእ​ርሱ በዐ​ይ​ኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተ​ራ​ቈ​ተና የተ​ገ​ለጠ ነው እንጂ በእ​ርሱ ፊት የተ​ሰ​ወረ ፍጥ​ረት የለም።


ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆም ዙፋን በሰማይ ቆሞአል፤ በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች