Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የሰው መንገድ በእግዚአብሔር ዐይኖች ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የሰው መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ግልጥ ነውና፤ እርሱ መሄጃውን ሁሉ ይመረምራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የሰው መንገድ በጌታ ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔር ሰው የሚያደርገውን ሁሉ ያያል፤ የሚሄድበትንም መንገድ ሁሉ ይመለከታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 5:21
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ በእ​ርሱ ዘንድ ፍጹም የሆ​ነ​ውን ያጸና ዘንድ ዐይ​ኖቹ በም​ድር ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታ​ሉና። አሁ​ንም ባለ​ማ​ወ​ቅህ በድ​ለ​ሃል፤ ስለ​ዚ​ህም ከዛሬ ጀምሮ ጦር​ነት ይሆ​ን​ብ​ሃል።”


አሁን ግን ኀጢ​አ​ቶ​ችን ቈጥ​ረ​ሃል፤ ከበ​ደ​ሌም እን​ዲ​ቱ​ንስ እንኳ አል​ረ​ሳ​ህም።


በታ​መ​መም ጊዜ መዳ​ንን ተስፋ አያ​ደ​ር​ግም። ነገር ግን እርሱ በሕ​ማሙ ይሞ​ታል።


እርሱ መን​ገ​ዴን የሚ​ያይ አይ​ደ​ለ​ምን? እር​ም​ጃ​ዬ​ንስ ሁሉ የሚ​ቈ​ጥር አይ​ደ​ለ​ምን?


እርሱ የሰ​ዎ​ችን ሥራ ይመ​ረ​ም​ራል፥ ከሚ​ሠ​ሩ​ትም ሁሉ ከእ​ርሱ የሚ​ሰ​ወር ምንም የለም።


“ምላ​ሳ​ች​ንን እና​በ​ረ​ታ​ለን፤ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ችን የእኛ ናቸው፥ ጌታ​ችን ማን ነው?” የሚ​ሉ​ትን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በጠ​ራ​ሁት ጊዜ ከጠ​ላ​ቶቼ እድ​ና​ለሁ።


የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉ ቦታ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችንም ይመለከታሉ።


ለእግርህ ቀና መሄጃ ሥራ፥ መንገዶችህንም አቅና።


በሕይወት መንገድም አትሄድም። መሮጫዋ ሰንከልካላ ነው፥ የሚታወቅም አይደለም።


ዐይ​ኖች በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ከፊ​ቴም አል​ተ​ሰ​ወ​ሩም፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከዐ​ይ​ኖች አል​ተ​ሸ​ሸ​ገም።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ሁሉ እንደ መን​ገ​ዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመ​ረ​ም​ራ​ለሁ፤ ኵላ​ሊ​ት​ንም እፈ​ት​ና​ለሁ።”


ሰው በስ​ውር ቦታ ቢሸ​ሸግ፥ እኔ አላ​የ​ው​ምን? ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንስ የሞ​ላሁ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ክፉ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፥ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ሚስ​ቶች ጋር አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና፥ ያላ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ንም ቃል በስሜ በሐ​ሰት ተና​ግ​ረ​ዋ​ልና። እኔም አው​ቃ​ለሁ፤ ምስ​ክ​ርም ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ክር ታላቅ በሥ​ራም ብርቱ ነህ፤ ስምህ ታላቅ የሆነ፥ ኀያል፥ ሁሉን ቻይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሁ​ሉም እንደ መን​ገ​ዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይ​ኖ​ችህ በሰው ልጆች መን​ገድ ሁሉ ተገ​ል​ጠ​ዋል።


ወን​ጀ​ላ​ቸ​ውን አንድ ያደ​ርጉ ዘንድ በል​ባ​ቸው እንደ አሰቡ ክፋ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ዐሰ​ብሁ፤ አሁ​ንም ክፋ​ታ​ቸው ከብ​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤ በደ​ላ​ቸ​ውም በፊቴ አለች።


እኛን በሚ​ቈ​ጣ​ጠር በእ​ርሱ በዐ​ይ​ኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተ​ራ​ቈ​ተና የተ​ገ​ለጠ ነው እንጂ በእ​ርሱ ፊት የተ​ሰ​ወረ ፍጥ​ረት የለም።


“በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዐይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል፦


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች