Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 4:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ልጆቼ ሆይ፤ የአባትን ምክር አድምጡ፤ ልብ ብላችሁ ስሙ፤ ማስተዋልንም ገንዘብ አድርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ልጆቼ ሆይ! የአባታችሁን ምክር ስሙ፤ በጥንቃቄ አዳምጡ፤ ማስተዋልንም ታገኛላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 4:1
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ​ዚ​ህም ከሰ​ማ​ነው ነገር ምን​አ​ል​ባት እን​ዳ​ን​ወ​ሰድ ለእ​ርሱ አብ​ዝ​ተን ልን​ጠ​ነ​ቀቅ ይገ​ባ​ናል።


የዐ​መፃ ምስ​ክ​ሮች ተነ​ሡ​ብኝ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ንም በእኔ ላይ ተና​ገሩ።


ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ትእዛዝ ቸል አትበል፤


ለመስማት ጆሮህን ወደ ጠቢባን ቃል አዘንብል፥ የእኔንም ቃል ስማ፥ መልካምንም ታውቅ ዘንድ ልብህን አቅርብ።


ልጄ ሆይ፥ ጥበቤን ተመልከት፤ ጆሮህም ወደ ቃሌ ያድምጥ፥


ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ በፍጻሜህ ጠቢብ ትሆን ዘንድ።


ጥበብን፦ “አንቺ እኅቴ ነሽ” በላት፥ ማስተዋልንም፦ “ወዳጄ” ብለህ ጥራት፥


ጥበብንና ተግሣጽን ለማወቅ፥ የጥበብንም ቃል ለማወቅ፥


እኛም የአ​ባ​ታ​ች​ንን የሬ​ካብ ልጅ የኢ​ዮ​ና​ዳ​ብን ቃል ባዘ​ዘን ነገር ሁሉ ታዝ​ዘ​ናል፤ እኛም ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ንም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ንም ዕድ​ሜ​አ​ች​ንን ሙሉ የወ​ይን ጠጅ አል​ጠ​ጣ​ንም፤


እና​ንት የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ኑ፥ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ ስሙም፤ አባ​ታ​ችሁ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አድ​ምጡ።


ዐዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል፤ የማይሰማ ልጅ ግን ይጠፋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች