Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ አምላክን ማወቅንም ታገኛለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በዚያ ጊዜ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ትረዳለህ፤ አምላክንም ማወቅ ታገኛለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የዚያን ጊዜ ጌታን መፍራትን ትገነዘባለህ፥ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ይህን ሁሉ ብታደርግ እግዚአብሔርን መፍራት ምን እንደ ሆነ ታውቃለህ፤ የአምላክንም ዕውቀት ታገኛለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 2:5
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።


እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ የሚ​ያ​ውቅ ልብ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በፍ​ጹ​ምም ልባ​ቸው ወደ እኔ ይመ​ለ​ሳ​ሉና ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


ሁሉ ከአ​ባቴ ዘንድ ተሰ​ጠኝ፤ ወልድ ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም፤ አብም ማን እንደ ሆነ ከወ​ልድ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም። ወልድ ግን ለወ​ደ​ደው ይገ​ል​ጥ​ለ​ታል።”


ነገር ግን የሚ​መ​ካው፦ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን፥ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ የማ​ደ​ርግ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሆ​ኔን በማ​ወ​ቁና በማ​ስ​ተ​ዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።


እን​ወ​ቀው፤ እና​ው​ቀ​ውም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ከ​ተል፤ እንደ ወገ​ግ​ታም ተዘ​ጋ​ጅቶ እና​ገ​ኘ​ዋ​ለን፤ በም​ድ​ርም ላይ እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ውና እንደ ኋለ​ኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመ​ጣል።


እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወን​ድ​ሙን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕወቅ ብሎ አያ​ስ​ተ​ም​ርም፤ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያው​ቁ​ኛ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። በደ​ላ​ቸ​ውን እም​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አላ​ስ​ብ​ምና።”


የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ የቅዱሳንም ምክር ዕውቀት ነው፥ ሕግንም ማወቅ ለልብ ደግ ነው።


ሰው​ንም፦ ‘እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ጥበብ ነው፤ ከክፉ መራ​ቅም ማስ​ተ​ዋል ነው’ ” አለው።


ብቻ​ህን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ የሆ​ንህ አን​ተን፥ የላ​ክ​ኸ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ናት።


እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ እኔንም የሚሹ ሞገስን ያገኛሉ።


በድ​ኅ​ነ​ታ​ችን መዝ​ገብ በሕግ ይሰ​በ​ስ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥበ​ብና ምክር፥ ጽድ​ቅም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህም የጽ​ድቅ መዝ​ገ​ቦች ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች