Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 18:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥ በኀያላንም መካከል ይለያል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ዕጣ ክርክርን ትከለክላለች፥ በኃያላንም መካከል ትበይናለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዕጣ መጣል ጠብን ያበርዳል፤ ሁለት ጠንካራ ተከራካሪዎችንም ይገላግላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 18:18
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ዚ​ህም ደግሞ በን​ጉሡ በዳ​ዊ​ትና በሳ​ዶቅ በአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም በሌ​ዋ​ው​ያ​ንና በካ​ህ​ናት አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት፥ ታላ​ላ​ቆች እንደ ታና​ናሽ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣ​ጣሉ።


ለሜ​ራ​ሪም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከሮ​ቤል ነገድ፥ ከጋ​ድም ነገድ፥ ከዛ​ብ​ሎ​ንም ነገድ፥ ዐሥራ ሁለት ከተ​ሞች በዕጣ ተሰጡ።


የሕ​ዝ​ቡም አለ​ቆች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ፤ ከቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ከዐ​ሥሩ ክፍል አንዱ በቅ​ድ​ስ​ቲቱ ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዘጠ​ኙም በሌ​ሎች ከተ​ሞች ይቀ​መጡ ዘንድ ዕጣ ተጣ​ጣሉ።


የበደለኛ ሰው በደሉ ሁሉ ወደ ጕያው ይመለሳል። ጽድቅ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


ከፍርድ በፊት ራሱን የሚከስስ ጻድቅ ነው፥ ያመጣው ባላጋራውም ይገሠጻል።


ወንድሙን የሚረዳ ወንድም እንደ ጸናችና ከፍ እንዳለች ከተማ ነው። በጽኑ መሠረትም እንደ ታነጸ ሕንጻ የጸና ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ እን​ዳ​ዘዘ ለዘ​ጠኙ ነገ​ድና ለእ​ኩ​ሌ​ታው በየ​ር​ስ​ታ​ቸው በዕጣ አከ​ፋ​ፈ​ሉ​አ​ቸው።


ሳኦ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ ዛሬ ያል​መ​ለ​ስ​ህ​ልኝ ስለ ምን​ድን ነው? ይህች በደል በእኔ፥ በልጄ በዮ​ና​ታ​ንም እንደ ሆነች አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተና​ገር። ዕጣው ይህን የሚ​ገ​ልጥ ከሆነ ለሕ​ዝ​ብህ ለእ​ስ​ራ​ኤል እው​ነ​ትን ግለጥ፥” አለ። ዕጣም በዮ​ና​ታ​ንና በሳ​ኦል ላይ ወጣ፤ ሕዝ​ቡም ነፃ ወጣ።


ሳኦ​ልም፥ “በእ​ኔና በዮ​ና​ታን መካ​ከል ዕጣ አጣ​ጥ​ሉን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕጣ ያወ​ጣ​በ​ትም ይሞ​ታል” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “እን​ዲህ ያለ ነገር አይ​ሆ​ንም” አሉት፤ ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን እንቢ አላ​ቸው። በእ​ር​ሱና በልጁ በዮ​ና​ታን መካ​ከ​ልም ዕጣ አጣ​ጣሉ። ዕጣ​ውም በልጁ በዮ​ና​ታን ላይ ወጣ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች