Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 17:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ጻድቅን ሰው ማዋረድ መልካም አይደለም። በእውነት ለሚፈርዱም መዋሸት መልካም አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ንጹሑን ሰው መቅጣት ተገቢ አይደለም፤ ሹሞችን ስለ ቅንነታቸው መግረፍ መልካም አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ጻድቅን መቅጣት፥ ጨዋ ሰውንም በጻድቅነቱ መምታት መልካም አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ንጹሑን ሰው መቀጫ ማስከፈል፥ ወይም ጨዋውን ሰው ማስገረፍ ተገቢ አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 17:26
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ ይህ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ገዛ ይህን ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም።”


አሁ​ንም ተነ​ሥ​ተህ ወጥ​ተህ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በል​ባ​ቸው የሚ​ገባ ነገር ንገ​ራ​ቸው። ዛሬ ወደ እነ​ርሱ ካል​ወ​ጣህ በዚች ሌሊት አንድ ሰው ስንኳ ከአ​ንተ ጋር የሚ​ያ​ድር እን​ዳ​ይ​ኖር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እም​ላ​ለሁ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትህ ጀምሮ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ ካገ​ኘህ መከራ ሁሉ ዛሬ የም​ታ​ገ​ኝህ መከራ እን​ድ​ት​ከ​ፋ​ብህ እን​ግ​ዲህ አንተ ለራ​ስህ ዕወቅ” አለው።


እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እር​ሱም በን​ጉሡ ዘንድ የተ​ሾመ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እነ​ዚ​ህም ሰዎች የሦ​ር​ህያ ልጆች በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመ​ል​ስ​በት” አላ​ቸው።


ኃጥኡን ጻድቅ፥ ጻድቁንም ኃጥእ ብሎ መፍረድ በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰና የተናቀ ነው።


የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም። በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥


የጭፍሮች ሴት ልጅ ሆይ፥ ጭፍሮችሽን አሁን ሰብስቢ፥ ከብቦ አስጨንቆናል፥ የእስራኤልን ፈራጅ ጕንጩን በበትር ይመታሉ።


ይህ​ንም ባለ​ጊዜ ከቆ​ሙት ሎሌ​ዎች አንዱ፥ “ለሊቀ ካህ​ናቱ እን​ዲህ ትመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለ​ህን?” ብሎ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በጥፊ መታው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች