Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 17:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ብልህ አገልጋይ አላዋቂዎች ጌቶችን ይገዛል፥ ከወንድማማች ጋርም ርስትን ይካፈላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ጠቢብ አገልጋይ በወራዳ ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ ከወንድማማቾቹም እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አስተዋይ ባርያ ነውረኛውን ልጅ ይገዛል፥ በወንድማማች መካከልም ርስትን ይካፈላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የጌታው ልጅ ወራዳ ከሆነ ብልኅ አገልጋይ በጌታው ልጅ ላይ የበላይነት ይኖረዋል፤ ከወንድማማቾቹም ጋር ርስት ተካፋይ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 17:2
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የተማረ ልጅ ብልህ ይሆናል። ሰነፍ ልጅ ግን ራሱን ተገዥ ያደርጋል። ብልህ ልጅ ከቃጠሎ ይድናል፤ ኀጢአተኛ ልጅ ግን በአውድማ ነፋስ የሚጨብጥ ይሆናል። ብልህ ልጅ በመከር ጊዜ ይሠራል። ሰነፍ ልጅ ግን በመከር ጊዜ ይተኛል።


ድሃና ጠቢብ ብላ​ቴና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ተግ​ሣ​ጽን መቀ​በል ከማ​ያ​ውቅ ከሰ​ነፍ ሽማ​ግሌ ንጉሥ ይሻ​ላል።


አባቱን የሚያዋርድ እናቱንም የሚያሳድድ፥ አሳፋሪና ጐስቋላ ልጅ ይሆናል።


አስተዋይ መልእክተኛ በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፤ በመልካም ጠባዩም ውርደትን ከራሱ ያርቃል።


ቤቱን የማያውቅ ሰው ነፋስን ይወርሳል፥ ሰነፍም ለጠቢብ ተገዥ ይሆናል።


ብዙ ደስታ ከሞላበትና ከክርክር ጋር የዐመፃ ፍሪዳ ካለበት ቤት ይልቅ፥ ከሰላም ጋር ደረቅ ቍራሽ ይሻላል።


ብርና ወርቅ በከውር እንዲፈተን፥ የተመረጡ ሰዎች ልብም በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች