Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የትሑት ሰው ሥራ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ነው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ለሰው መንገዱ ሁሉ ንጹሕ መስሎ ይታየዋል፤ መነሻ ሐሳቡ ግን በእግዚአብሔር ይመዘናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰው መንገድ ሁሉ በዐይኖቹ ፊት ንጹሕ ነው፥ ጌታ ግን መንፈስን ይመዝናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል የሆነ ሊመስለው ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ዓላማውን ይመዝናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 16:2
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰው ሁሉ ለራሱ ጻድቅ መስሎ ይታያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያቀናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ፊቱን፥ የቁ​መ​ቱ​ንም ዘለ​ግታ አትይ፤ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይ​ምና ናቅ​ሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልብን ያያል” አለው።


እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ለሰው ይም​ሰል ትመ​ጻ​ደ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ች​ሁን ያው​ቃል፤ በሰው ዘንድ የከ​በረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ናቀ ይሆ​ና​ልና።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ሁሉ እንደ መን​ገ​ዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመ​ረ​ም​ራ​ለሁ፤ ኵላ​ሊ​ት​ንም እፈ​ት​ና​ለሁ።”


እነሆ፥ ይህን አላውቅም ብትል፥ እግዚአብሔር የሁሉን ልብ እንዲያውቅ ዕወቅ። ለሁሉ እስትንፋስን የፈጠረ እርሱ ሁሉን ያውቃል። ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፍለዋል።


እንደ ሣር ፈጥ​ነው ይደ​ር​ቃ​ሉና፥ እንደ ለመ​ለመ ቅጠ​ልም ፈጥ​ነው ይረ​ግ​ፋ​ሉና።


የሰው መንገድ በእግዚአብሔር ዐይኖች ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና።


ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን የሲኦል ጕድጓዶችን ይመለከታል።


የጻ​ድ​ቃን መን​ገድ የቀና ትሆ​ና​ለች፤ የቅ​ኖ​ችም መን​ገድ ትጠ​ረ​ጋ​ለች።


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


“በትያጥሮንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዐይኖች ያሉት በእቶንም የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል፦


አት​መኩ፤ የኵ​ራት ነገ​ሮ​ች​ንም አት​ና​ገሩ፤ ፅኑዕ ነገ​ርም ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ዐዋቂ ነውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዙፋ​ኑን ያዘ​ጋ​ጃል።


የሰነፎች መንገድ በፊታቸው የቀናች ናት፤ ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “አህ​ያ​ህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መን​ገ​ድህ በፊቴ ቀና አል​ነ​በ​ረ​ምና ላሰ​ና​ክ​ልህ ወጥ​ቼ​አ​ለሁ፤


በእ​ጃ​ቸ​ውም ውኃ ወደ አፋ​ቸው አድ​ር​ገው የጠ​ጡት ቍጥር ሦስት መቶ ሆነ፤ የቀ​ሩት ሕዝብ ግን ውኃ ሊጠጡ በጕ​ል​በ​ታ​ቸው ተን​በ​ረ​ከኩ።


በዚ​ያም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ ሰውም ሁሉ በፊቱ መል​ካም መስሎ የታ​የ​ውን ያደ​ርግ ነበር።


ብርና ወርቅ በከውር እንዲፈተን፥ የተመረጡ ሰዎች ልብም በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች