Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ቍጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ትዕግሥተኛ ሰው ግን የሆነውን ስንኳ ያጠፋል። ትዕግሥተኛ ሰው ክርክርን ያጠፋል፥ ኀጢአተኛ ሰው ግን ጠብን ፈጽሞ ያነሣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ግልፍተኛ ሰው ጠብ ያነሣሣል፤ ታጋሽ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ቁጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፥ ትዕግሥተኛ ሰው ግን ጸጥ ያሰኘዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ቊጣ ጭቅጭቅን ያነሣሣል፤ ትዕግሥት ግን ጠብን ያበርዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 15:18
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ለይ​ሁዳ ሰዎች መል​ሰው፥ “በን​ጉሡ ዘንድ ለእኛ ዐሥር ክፍል አለን፤ ከእ​ና​ን​ተም እኛ እን​ቀ​ድ​ማ​ለን፤ እኛም በኵር ነን፤ ለዳ​ዊ​ትም ከእ​ና​ንተ እኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤ ስለ​ምን ናቃ​ች​ሁን? ንጉ​ሡ​ንስ እን​መ​ል​ሰው ዘንድ ከእ​ና​ንተ የእኛ ቃል አይ​ቀ​ድ​ም​ምን?” አሏ​ቸው። የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ቃል ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነ​ከረ።


ቍጣ ጥልን ያነሣሣል። ፍቅር ግን የማይጣሉትን ሁሉ ይሸፍናቸዋል።


ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤ ትዕግሥት የጐደለው ሰው ግን ሰነፍ ነው፤


ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ የለዘበ ቃል ቍጣን ይመልሳል፥ ሻካራ ቃል ግን ጠብን ያነሣሣል።


የሰነፎች መንገዶች እሾህ የተከሰከሰባቸው ናቸው፥ የጽኑዓን መንገዶች ግን ጥርጊያ ናቸው።


የንጉሥ ቍጣ እንደ መልአከ ሞት ነው፤ ብልህ ሰው ግን ያቈላምጠዋል።


ጠማማ ሰው ክፋትን ይዘራል፥ የሐሰት መብራት ክፉዎችን ታቃጥላቸዋለች፥ ወዳጆችንም ትለያለች።


ከቍጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፥ ከነዝናዛም ጓደኛ ጋር አትኑር።


ትዕ​ግ​ሥት ታላ​ቁን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና የገዢ ቍጣ የተ​ነ​ሣ​ብህ እንደ ሆነ ስፍ​ራ​ህን አት​ል​ቀቅ።


የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፤የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች