Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 14:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የዐዋቂዎች ጥበብ መንገዳቸውን ታውቃለች፤ የሰነፎች ስንፍና ግን ወደ ስሕተት ይመራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የአስተዋዮች ጥበብ መንገዳቸውን ልብ ማለት ነው፤ የሞኞች ቂልነት ግን መታለል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የብልህ ሰው ጥበብ መንገዱን ያስተውል ዘንድ ነው፥ የሰነፎች ስንፍና ግን ሽንገላ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የብልኅ ሰው ጥበብ መንገዱን እንዳይስት ያደርገዋል። ሞኝን ሰው ግን ሞኝነቱ መንገዱን እንዲስት ያደርገዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 14:8
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኀጢ​አ​ተ​ኛም አይቶ ይቈ​ጣል፥ ጥር​ሱ​ንም ያፋ​ጫል፥ ይቀ​ል​ጣ​ልም፤ የኃ​ጥ​ኣ​ንም ምኞት ትጠ​ፋ​ለች።


መኖ​ሪ​ያዬ የራቀ እኔ ወዮ​ልኝ፤ በዘ​ላን ድን​ኳ​ኖች አደ​ርሁ።


አፋ​ቸው ከንቱ ነገ​ርን ከሚ​ና​ገር፥ ቀኛ​ቸ​ውም የዐ​መፃ ቀኝ ከሆነ አስ​ጥ​ለኝ።


ክፉ ሰው የበደልን ሥራ ይሠራል፤ ለጻድቃን ዘር ግን የታመነ ዋጋ አለው።


የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፤ ኃጥኣን ግን ሽንገላን ያስተምራሉ።


የአላዋቂ ሰው መንገዶች ጠማሞች ናቸው፤ ብልህ ሰው ግን አቅንቶ ይሄዳል።


የዚያን ጊዜ ጽድቅንና ፍርድን ታውቃለህ፤ መልካም መንገድንም ሁሉ ታቃናለህ።


እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፥ በፍርድ ጎዳና መካከልም እመላለሳለሁ፥


እኔም ብር​ሃን ከጨ​ለማ እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ እን​ዲሁ ከአ​ላ​ዋቂ ይልቅ ለብ​ልህ ብልጫ እን​ዳ​ለው ተመ​ለ​ከ​ትሁ።


ለብ​ልህ ከአ​ላ​ዋቂ ጋር ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ የለ​ውም፤ እነሆ፥ ዘመን ይመ​ጣ​ልና ሁሉም ይረ​ሳል፤ ብል​ህስ ከአ​ላ​ዋቂ ጋር እን​ዴት ይሞ​ታል?


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ! ዐይ​ን​ሽን አን​ሥ​ተሽ እነ​ዚ​ህን ከሰ​ሜን የሚ​መ​ጡ​ትን ተመ​ል​ከቺ፤ ለአ​ንቺ የሰ​ጠ​ሁሽ መንጋ፤ የክ​ብር በጎ​ችሽ ወዴት አሉ?


የዚህ ዓለም ጥበብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ድን​ቍ​ርና ነውና፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “ጠቢ​ባ​ንን የሚ​ገ​ታ​ቸው ተን​ኰ​ላ​ቸው ነው።”


የቀ​ድሞ ጠባ​ያ​ች​ሁን ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ ይህ​ንም ስሕ​ተት በሚ​ያ​መ​ጣው ምኞት ስለ​ሚ​ጠ​ፋው ስለ አሮ​ጌው ሰው​ነት እላ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም ሰነ​ፎች አት​ሁኑ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ አስ​ተ​ውሉ እንጂ።


ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች እያሳቱና እየሳቱ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ።


ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች