Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 13:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የደጋግ ሰዎች ምኞት ነፍስን ያድናል፤ የሰነፎች ሥራ ግን ከዕውቀት የራቀ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ምኞት ስትፈጸም ነፍስን ደስ ታሰኛለች፤ ሞኞች ግን ከክፋት መራቅን ይጸየፋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የተፈጸመች ፈቃድ ሰውነትን ደስ ታሰኛለች፥ ሰነፎች ግን ከክፉ መራቅን ይጸየፋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የተመኙትን ነገር ማግኘት እጅግ ደስ ያሰኛል፤ ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ግን ከክፉ ነገር መራቅ አይፈልጉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 13:19
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም፥ “ዐይኔ እያየ ዛሬ በዙ​ፋኔ ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን ዘር የሰ​ጠኝ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” አለ።


ሰው​ንም፦ ‘እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ጥበብ ነው፤ ከክፉ መራ​ቅም ማስ​ተ​ዋል ነው’ ” አለው።


ለወ​ዳ​ጆቼና ለወ​ን​ድ​ሞቼ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ አደ​ረ​ግሁ፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ለ​ቅ​ስና እን​ደ​ሚ​ተ​ክዝ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደ​ረ​ግሁ።


ከሚበለጽግና በተስፋ ከሚቈይ ሰውነቱን ሊረዳ የሚጀምር ይሻላል። መልካም ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ናት።


ትምህርት ድህነትንና ጕስቍልናን ያስወግዳል፤ ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ይከብራል።


ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ ከአላዋቂዎች ጋር የሚሄድ ግን አላዋቂ ይሆናል።


የሕይወት መንገዶች ከክፉ ያርቃሉ፤ የጽድቅ ጎዳና የዘመን ብዛት ነው። ትምህርትን የሚቀበል በበጎ ይኖራል። ተግሣጽን የሚጠብቅም ብልሃተኛ ይሆናል። መንገዶቹን የሚጠብቅ ሰውነቱን ይጠብቃል፥ ሕይወትንም የሚወድድ አፉን ይጠብቃል።


እግዚአብሔርን የሚፈልግ ዕውቀትን ከጽድቅ ጋር ያገኛል፥


በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ እግዚአብሔርን ፍራው፥ ከክፋትም ሁሉ ራቅ፤


ከእ​ነ​ር​ሱም ጥቂት እልፍ ብዬ ያን​ጊዜ ነፍሴ የወ​ደ​ደ​ች​ውን አገ​ኘ​ሁት፥ ያዝ​ሁ​ትም፤ ወደ እና​ቴም ቤት፥ ወደ ወላጅ እና​ቴም እል​ፍኝ እስ​ካ​ገ​ባው ድረስ አል​ተ​ው​ሁ​ትም።


ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች