Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 10:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ኃጥእ እንደ ዐውሎ ነፋስ ኅልፈት ይጠፋል፤ ጻድቅ ግን ተሰውሮ ለዘለዓለም ይድናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ዐውሎ ነፋስ ሲነሣ ክፉዎች ተጠራርገው ይወሰዳሉ፤ ጻድቃን ግን ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ዐውሎ ነፋስ ሲያልፍ ክፉ ሰው አይገኝም፥ ጻድቅ ግን የዘለዓለም መሠረት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ዐውሎ ነፋስ በሚነሣበት ጊዜ ክፉዎች ተጠርገው ይወሰዳሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን ዘወትር ጸንተው ይኖራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 10:25
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ወደ መን​ገዴ እንደ ምመ​ለስ እተ​ማ​መ​ና​ለሁ፤ እጆ​ችም የነጹ ናቸ​ውና፤ ደስ​ታ​ዬን አገ​ኛ​ታ​ለሁ።


እንደ ሕልም ይበ​ር​ራል፤ እር​ሱም አይ​ገ​ኝም፤ ሲነ​ጋም እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ እንደ ሌሊት ራእይ ይሰ​ደ​ዳል።


በነ​ፋ​ስም ፊት እንደ ገለባ፥ አውሎ ነፋ​ስም እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ይሆ​ናሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ምርኮ በመ​ለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስ​ተ​ኞች ሆንን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የር​ስቴ ዕድል ፋን​ታና ጽዋዬ ነው፥ ርስ​ቴን የም​ት​መ​ልስ አንተ ነህ።


የአ​ም​ላኬ ይቅ​ር​ታው ይድ​ረ​ሰኝ አም​ላኬ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አሳ​የኝ።


ኀይ​ሌን ወደ አንተ አስ​ጠ​ጋ​ለሁ፥ አንተ አም​ላ​ኬና መጠ​ጊ​ያዬ ነህና።


ጭቅጭቅ ድንገት በመጣባችሁ ጊዜ፥ እንደዚሁም ጥፋታችሁ እንደ ዓውሎ ነፋስ በመጣባችሁ ጊዜ፥ ችግርና ምርኮ በደረሰባችሁ ጊዜ፥ እኔ ከዚያ አለሁ።


ጻድቃን ለዘለዓለም አይናወጡም፤ ኃጥኣን ግን በምድር ላይ አይቀመጡም።


ከዐመፃ የማይርቅ ሰው ይጠፋል፤ የጻድቃን ሥር ግን አይነቀልም።


ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥ የጻድቃን ቤቶች ግን ጸንተው ይኖራሉ።


በእ​ር​ሱም ላይ ዛፉ​ንና ሣሩን፥ የማ​ይ​ቈ​ጠር ሌላ​ው​ንም ብዙ ፍጥ​ረት የፈ​ጠረ እርሱ ነው። ነፋ​ስም በነ​ፈ​ሰ​ባ​ቸው ጊዜ ይደ​ር​ቃሉ፤ ዐውሎ ነፋ​ስም እንደ ገለባ ይጠ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።


እኔም እልሃለሁ፤ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚችም ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።


በነ​ቢ​ያ​ትና በሐ​ዋ​ር​ያት መሠ​ረት ላይ ታን​ጻ​ች​ኋ​ልና የሕ​ን​ጻው የማ​ዕ​ዘን ራስ ድን​ጋ​ይም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው፤


ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች